በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኮሚቴ አቋቁመን ሁኔታውን እያጣራን ነው” አቶ ፍሰሃ ጋረደው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር


ከፌስ ቡክ የተገኘ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በሚል አከራካሪ የኾነ ፎቶ
ከፌስ ቡክ የተገኘ ደቡብ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን በሚል አከራካሪ የኾነ ፎቶ

ካለፈው እሁድ ጀምሮ በማኅበራዊ ሚድያ ሲሰራጩ የቆዩት፤በደቡብ ክልል በኦሞ ዞን የሚገኙ አራት ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ እግር ለእግርና አንገት ለአንገት በቃጫ ገመድ ታሥረውና እንግልት ደርሶባቸው የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን በተመለከተ የክልሉ ፖሊስ ኮሚቴ አቋቁሞ እያጣራ እንደኾነ ሲገልፅ አንድ የሱርማ ነዋሪ ፤ ያስቸገረን ወንጀለኛን በገመድ አስሮ መያዝ በሱርማ የተለመደ እንደኾነ ይናገራሉ፡፡ ጽዮን ግርማ ተከታዩን ዘግባለች፡፡

ካለፈው እሁድ ጀምሮ በደቡብ ክልል በኦሞ ዞን የሚገኙ አራት ኢትዮጵያዊያን እርስ በርስ ፣ እግር ለእግርና አንገት ለአንገት በቃጫ ገመድ ታሥረውና እንግልት ደርሶባቸው የሚያሳዩ ፎቶግራፎች በማኅበራዊ ሚድያ ተሰራጭቷል፡፡ ፎቶ ግራፎቹ በማኅበራዊ ሚድያ ላይ ከወጡ በኋላ የታሣሪዎቹ ማንነት አጨቃጭቂ ድርጊቱም በበርካቶች ዘንድ አሳዛኝ ኾኖ ሰንብቷል፡፡

አንድ የሱርማ ነዋሪ ፤ ያስቸገረን ወንጀለኛን በገመድ አስሮ መያዝ በሱርማ የተለመደ እንደኾነ ይናገራሉ፡፡ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ፍሰኃ ጋረደው በበኩላቸው ኮሚቴ አቋቁመው ሁኔታውን እያጣሩ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ፍስሃ ጋረደውን ጽዮን ግርማ አነጋግራ ተከታዩንዘግባለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“ኮሚቴ አቋቁመን ሁኔታውን እያጣራን ነው” አቶ ፍሰሃ ጋረደው የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:21 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG