በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይረክተር ለመሆን መወዳደር ጀምረዋል


የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮሃስ አድኖም
የቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮሃስ አድኖም

​“ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በአሁኑ ወቅት ያሉትንና ለወደፊት በጤና ጉዳይ ላዩ አደጋ የሚጥሉትን ችግሮች የመቋቋም ራእይና ተመክሮ ያላቸው ናቸው" ሲሉ የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተ-ብርሀን አድማሱ አስገንዝበዋል።

ቀድሞ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የነበሩት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይረክተር ለመሆን መወዳደር ጀምረዋል። የመጀመርያው አፍሪካዊ ተወዳዳሪ ሆነዋል።

ዶክተር ቴዎድሮስ ጄኔቫ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት ውድድሩን የጀመሩት አለም አቀፍ ሚድያ በተገኘበት እንደሆነ ታውቋል። አለም አቀፍ የጤና ድርጅት ጄኔቫ ውስጥ አመታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። አዲስ የድርጅቱ ዋና ዳይረክተር የሚሰየመው ከአንድ አመት በኋላ ነው።

እንደሚታወቀው አፍሪቃና ሌሎች ታዳጊ ሀገሮች ናቸው አብዛኛውን ችግር የሚሸከሙት። ያም ሆኖ አፍሪካ ወይም ሌላ ታዳጊ ሃገር የአለም ጤናን ከዚሁ አንጻር ለማየይት የሚችሉበትና ያላቸውን ችግር መሰረት ሊረዱ የሚችሉት ወገኖች እድል አላገኙም።
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደሚወዳደሩ ባስታወቁበት ወቅት በበርካታ ደጋፊ ሰራተኞችና ከፍተኛ ቦታ ባላቸው አፍሪካውያን ባለስልጣኖች ታጅበው ነው። የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበርና የአልጀርያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አብረዋቸው ከቆሙት ሰዎች መካከል ነበሩ። ብቃታቸውንና የረጅም ጊዜ ሙያዊ ልምዳቸውን በመጥቀስ የአለም የጤና ድርጅት ኃላፊ እንዲሆኑ እንደሚደግፉ ለመግለጽ ነበር ደጋፊዎችና ከፍተኛ የአፍሪካ ባለስልታኖች አብረዋቸው የቆሙት።

​“ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በአሁኑ ወቅት ያሉትንና ለወደፊት በጤና ጉዳይ ላይ አደጋ የሚጥሉትን ችግሮች የመቋቋም ራእይና ተመክሮ ያላቸው ናቸው" ሲሉ የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተ-ብርሀን አድማሱ አስገንዝበዋል። ዶክተር ቴዎድሮስ ለአህጉሪቱና ለአለም ፍትህ ማምጣት ብቻ ሳይሆን የአለም የጤና ድርጅት በበለጠ ተገቢነት ያለው ተቋም እንዲሆን አድርገው የመምራት ብቃት አላቸው ሲሉም ዶክተር ከሰተ-ብርሃን አስረድተዋል።

የአለም የጤና ድርጅት ከተመሰረተ ወደ 70 አመታት የተጠጋ ቢሆንም አፍሪካዊ ዋና ዳይረክተር ኖሮት አያውቅም። አሁን ታድያ ስለወባ በሽታ ባደረጉት ጥናትና ምርምር አለም አቀፍ እውቅና ያገኙት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ይህን ለመለወጥ እየተወዳደሩ ነው።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ታድያ በሚከተለው አባባል አጠቃለውታል።

“እንደሚታወቀው አፍሪቃና ሌሎች ታዳጊ ሀገሮች ናቸው አብዛኛውን ችግር የሚሸከሙት። ያም ሆኖ አፍሪካ ወይም ሌላ ታዳጊ ሃገር የአለም ጤናን ከዚሁ አንጻር ለማየይት የሚችሉበትና ያላቸውን ችግር መሰረት ሊረዱ የሚችሉት ወገኖች እድል አላገኙም።”ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይረክተር ለመሆን መወዳደር ጀምረዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG