በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ደቡብ አፍሪካ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ከሚሄዱ 7 ኢትዮጵያዊያን አንዱ ለአቅም ያልደረሰ አዳጊ ነው/ናት


ከ20ሽህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በርካታ የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያመሩ IOM ይገምታል።

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችና ፍልሰተኞች ምስራቅ አፍሪካን አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያደርጉት ጉዞ፤ በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች እጅ በርካታ ወከባና ወንጀል የበዛበት አደገኛ መንገድ ነው።

ኬንያንና ታንዛንያን አልፈው በማላዊም እንዲሁ ጥቂቶቹ በቁጥጥር ስር ሲውሉ፤ የሚበዙት ደግሞ ወደ ቀጣዩ ሐገር ያመራሉ። በዛምቢያ በኩል ወይንም ሞዛምቢክን አቋርጠው ወደ ዝምባብዌ ይደርሳሉ።

ዝምባብዌና ደቡብ አፍሪካ ድንበር ስለሚጋሩ፤ በዚያ ሾልከው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይገባሉ ማለት ነው። በዚህ አስቸጋሪ መንገድ ህይወታቸውን ለአደጋ ጥለው የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 20ሽህ እንደሚደርስ የዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) ይገምታል።

በአጠቃላይ በማላዊ በሚገኙ በእስረኛ በተጨናነቁ ፍርድ ቤቶች በዚህ ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ታስረው የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 442 እንደሆነ የIOM መረጃ ያትታል።

ወደ ማላዊ የሚደርሱት ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች፤ በእስር ቤት ሳሉ ለህመምና ለምግብ እጥረት ተጋልጠው እንደቆዩም የዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (MSF) ይገልጻል።

በማላዊ ያለውን ሁኔታ ያብራሩት የIOM ወኪል ስቴፈኔ ትሮቸር በየሳምንቱ በቁጥጥር ስር እየዋሉ የሚገኙት በርካታ ኢትዮጵያዊያን መካከል ብቻቸውን የሚጓዙ 18 ዓመት ያልሞላቸው ህጻናት መበራከታቸው እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።

በIOM አኃዝ መሰረት በጸጥታ ሀይሎች ከሚያዙት 7 ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ/አንዷ አዳጊ ህጻን ነው/ናት።

እስረኞቹን ወደሀገራቸው ለመመለስ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ከማላዊና የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም በውጭ ሀገር ከሚኖሩ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት፤ እስረኞቹ ወደ ሀገራቸውን እንዲመለሱ ይረዳል።

ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው ይደምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ወደ ደቡብ አፍሪካ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ከሚሄዱ 7 ኢትዮጵያዊያን አንዱ ለአቅም ያልደረሰ አዳጊ ነው/ናት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:00 0:00

XS
SM
MD
LG