በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር 15 ደርሷል

የጋምቤላ ክልል ካርታ
የጋምቤላ ክልል ካርታ

በጋምቤላ ከተማ በስተምሥራቅ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ጃዊ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 15 መድረሱን ነዋሪዎች ተናገሩ። በሥራ ላይ እያለ በድንጋይ እንደተወገረ የሚናገረው መብራቱ የተባለ አንድ የቀን ሠራተኛ፤ጊዚያዊ ሕክምና በነጻ ቢያገኝም መድኃኒት የገዛው በግሉ ተበድሮ እንደኾነ ይናገራል። ተጨማሪ ሕክምና አግኝቶ ከሕመሙ ማገገም ፍላጎቱ እንደኾነ ይገለጻል።

ጃዊ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር /ፋይል ፎቶ/
ጃዊ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር /ፋይል ፎቶ/

የጋምቤላ ክልል መንግስት ሟቾቹ ዐስር ናቸው ይላል። የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች “በአገራችን እንዴት እንዲህ ያለ አሰቃቂ አደጋ ይደርስብናል?” በሚል ቅዳሜና እሁድ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር። ነዋሪዎቹ ሰልፉ በመከላከያና በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት እንዲቆም መደረጉንም ይናገራሉ። ከአደጋው ያመለጡና አሁን በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ወጣቶችም ሰላጋጠማቸው አደጋ ይናገራሉ።

ጽዮን ግርማ ይህን በተመለከተ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

በጋምቤላ የሟቾች ቁጥር 15 ደርሷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG