በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ


በቺካጎ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ
በቺካጎ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ

በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሞኑ እንቅስቃሴ ወቅት ፈጽሟል ያሏቸውን የመብት ጥሰቶች በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

የተቃውሞ ሰልፎቹ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ባለፈው ሳምንት፣ ለንደን በትናንቱ ዕለት፣ ዛሬ ደግሞ በቺካጎና በጄኔቫ ተካሂደዋል።

በለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ
በለንደን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰልፍ

በለንደን ሰልፈኞቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈጸማል ያለቱን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ በመቃወም የተካሄደው ትዕይንተ-ሕዝብ ሰላማዊና በጥሩ መንፈስ የተካሄደ፣ ኃላፊነትም በተሞላበት ሁኔታ መከናወኑን አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮች መካከልም፣ የእንግሊዝ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቁም፣ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፣ ጋዜጠኞችን ማዋከብና ማሰር ይቁም፣ ወዘተ የሚሉ ይገኙባቸዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG