በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ምንዛሪ አራት ሚሊየን ብር አግኝተው የመለሱት ኢትዮጵያዊ ባሜሪካ


አቶ አዳም ሰሎሞን ወልደማርያም
አቶ አዳም ሰሎሞን ወልደማርያም

አዳም ሰሎሞን ወልደማርያም በኔቫዳዋ ላስ ቬጋስ ከተማ ታክሲ ነጂ ናቸው፡፡ በቅርቡ 221 ሺህ 510 የአሜሪካ ዶላር እርሣቸው የሚይዙት መኪና ውስጥ ተረስቶ አግኝተው ለባለቤቶቹ መልሰዋል፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:07:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



“የሚሰማኝ እርካታና ደስታ ነው” አሉ መርካቶ አውቶቡስ ተራ አካባቢ ተወልደው፣ አራዳ ሠፈረ ሰላም ያደጉት አቶ አዳም ሰሎሞን፡፡ ወሰን ሰገድ እና ኮልፌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ተምረዋል፡፡ እንግዲህ ከቤተሰቦቻቸው ሌላ እንዲህ ዓይነት አካባቢና ዙሪያ ገባ ነው አቶ አዳምን ኮትኩቶ ያበቀላቸው፡፡
ደግሞም ወደ አሜሪካ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት መጡና በሜሪላንድና በዋሽንግተን ዲ.ሲ. አካባቢ አንድ ሁለት ዓመት ኖረው ሥራ የተሻለ ነው ብለው ጓደኞቻቸው ወደመከሯቸው ወደ ላስ ቬጋስ ደግሞ ገሠገሡ፡፡
እነሆ በሰባት ዓመታቸው ይህንን ገድል ሠሩና በአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን አደባባይ ላይ ዋሉ፡፡ “ታማኙ ኢትዮጵያዊ ታክሲ ነጂ” ተባሉና እራሣቸውንም የሃገራቸውንም ስም በክብር አስጠሩ፡፡
ብዙዎች “ጀግና” ሲሏቸው ብዙዎች ደግሞ እንደሞኝም የቆጠሯቸው ነበሩ፡፡ “አራት ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር ነው፤ ገንዘቡ ደግሞ የተረሣው የሕዝብ ማመላለሻ ውስጥ ነው፤ ለምን አላስቀሩትም ነበር?” ተብለው ሲጠየቁ “እንዲህ ዓይነት ነገር በውስጤ የለም፤ አልለመድኩትም” ነበር መልሣቸው፡፡
አቶ አዳም ሁለት ሺህ ዶላር በሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህንን መጠን ከመለሱት ገንዘብ ጋር ያስተያይዋል፡፡ “ምን ይሰማዎታል በዚህ አቶ አዳም?” መልስ፡- “በኩባንያችን ሕግ መሠረት - የሥነ-ምግባር ደንብ እንዲሉ ነው - መኪና ውስጥ የተረሣ ማንኛውም ነገር ለኩባንያው መመለስ አለበት፤ ደግሞም ሰዎቹ ምንም ያለመስጠትም አማራጭ ነበራቸው፡፡ ኩባንያዬን አስፈቅደው ነው የሰጡኝ፡፡”
ለማንኛውም ዛሬ አቶ አዳም ሰሎሞን ወልደማርያም በተግባራቸው የረኩና የተደሰቱ ናቸው፡፡
ቃለ-ምልልሱን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG