በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

13ኛው የዓለም ማኅበረሰብ ጤና ጉባዔ በአዲስ አበባ


አዲስ አበባ ላይ የተጠራው 13ኛው የዓለም ጤና ጉባዔ ከመቶ በላይ ሃገሮች የተወከሉ ባለሙያዎችን ማሰባሰሰቡ ተነግሯል፡፡

በገቢ ክፍፍል ፍትሃዊነት “ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ ሀገሮች ሁሉ በተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ተናግረዋል። በጤና አገልግሎት ሥርጭቱም ተመሳሳይ ገፅታ እንዳለ ተጠቁሟል።

የማኅበረሰብ ጤና አጠባበቅ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ተካፋዮች የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ተቋማትን እንደሚጎበኙም ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከአንድ መቶ አሥራ ስድስት ሃገሮች የተወከሉ የጤና ባለሙያዎች የተወከሉበት የአዲስ አበባው ጉባዔ ተሣታፊዎች ትኩረት በሃብታምና በድኃ ሃገሮች መካከል ያለውን የጤና ጥበቃ ጥራት ክፍተት ማጥበብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከር መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተሻለ ክፍያ የሚያስገኙ ሥራዎችን ለመፈለግ የዶክተሮችና የነርሶች ወደበለፀጉት መፍለስ በማደግ ላይ ያሉትን እየጎዳቸው እንደሆነም እየተነገረ ነው፡፡

ለዝርዝር መረጃ ዘገባዎቹን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG