በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጥኞች ምህረት ለመጠየቅ ወሰኑ


Martin Schibbye እና Johan Person ባለፈው ሰኔ ወር በሶማልያ ክልል የተያዙት በህገ-ወጥነት ከተፈረጀው የኦጋደን ብሄራዊ የሐርነት ግንባር ተዋጊዎች ጋር ይጓዙ በነበረበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል። ሶስት ዳኞች የተሰየሙበት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋዜጦኞቹ ከታገደው ቡድን ጋር ያላቸው መተሳሰር ከተለመደው የጋዜጠኝነት አሰራር የዘለለ ነው። ለአሸባሪነት ድጋፍ እንዳልቸውም ያመለክታል የሚል ብይን ሰጥቷል።

ሁለቱ ጋዜጠኞች ታድያ "በኢትዮጵያ የጸጋና የምህረት ባህል ስላለ በዚሁ ባህል ላይ መተማመኑን መርጠናል።” በማለት ይግባኝ ማለቱን ትተው ምህረት ለመጠያቅ እንደወሰኑ የፐርሰን አባት Kjell Persson ከስዊድን በስልክ እንደትናገሩ ተገልጿል

ይኸው ፌደራላዊ ፍርድ ቤት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውን ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከአሸባሪነት ጋር በተያያዘ የተከሰሱበት የፍርድ ሂደትን እያዳመጠ ነው። ሁሉም ተከሳሾች የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ዲሞክራስያዊ ግንባር መንግስትን በግልጽ የሚነቅፉ ናቸው።

XS
SM
MD
LG