በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መድረክ ተቃዋሚዎችን በፈጠራ ወንጀል መክሰስና ሕዝብን ማሸበር ይቁም ሲል መግለጫ አወጣ


በኤርትራና ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ተሙዋጋች ድርጅት Amnesty International መረጃ አጠናቃሪ ክሌር በስተን ስለጸረ ሽብር ሕጉ የተናገሩትን አካተናል

በጽሑፍ የወጣዉ መግለጫ የኢሃዴግ መንግስት፣ ጠንካራ ተቃዋሚዎች ናቸዉ ወይም ይሆናሉ ለሚላቸዉ የአገሪቱ የፖለቲካ ሃይሎች የተለያዩ ሰሞችን እየፈጠረ ከህጋዊ መድረክ የማስወጣት አባዜ የያዘዉ ገና ከጥዋቱ ስልጣን እንደተቆናጠጠ ነበር ይላል። ይህን የገዢዉ ፓርቲ ብልሃትና ባህሪ ነዉ የሚለዉን አካሄድ ኢሃዴግ ስልጣን ከያዘበት ከሺ983 ዓም ጀምሮ እስከ ሁለት ሺህ ሁለት ዓመት ምህረት ምርጫ ድረስና ከዚያም ወዲህ ፈጽሟቸዋል ያላቸዉን ወንጀሎች ይዘረዝራል።

በተለይ ባሁኑ ጊዜ በመድረክ አባል ድርጅቶች አባላት ላይ የሽብርተኝነትን ክስ እየመሰረተ መሆኑን መግለጫዉ ጠቅሶ፣ ኢሃዴግ ይህንን ድራማ ለመሥራት የተገደደዉ መድረክንና አባል ድርጅቶችን ከህዝቡ ለመነጠል አስቦ ነዉ ይላል።

ይህ እርምጃ ገዢዉ ፓርቲ የፈለገዉን ዉጤት የሚያመጣ አይመስለኝም ያሉት የመድረክ አመራር አባል ዶክተር መረራ ጉዲና የሰጡትን ሰፊ ገለጻ ለዘጋቢአችን መለስካቸዉ ተከታትሎ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ከዚህ ቀደም ብሎ በጸረ ሽብር ሕግ ስለሚከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሰጡትን ገለጻና፥ በኤርትራና ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሰብአዊ መብት ተሙዋጋች ድርጅት Amnesty International መረጃ አጠናቃሪ ክሌር በስተን ስለጸረ ሽብር ሕጉ የተናገሩትን አካተናል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG