በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልመና፣ የጎዳና ኑሮና የጎዳና ስራ በአዲስ አበባ


ልመና፣ የጎዳና ኑሮና የጎዳና ስራ በአዲስ አበባ
ልመና፣ የጎዳና ኑሮና የጎዳና ስራ በአዲስ አበባ

አካለ ስንኩልነት፣ ድህነት፣ ከአየር ንብረት መዛባትና ከሚታረስ መሬት እጥረት ጋር በተያያዘ ከገጠር ወደ ከተሞች የነዋሪዎች ፍልሰት በጎዳና ላይ ለሚታየው የተረጂ ቁጥር መበራከት ዋነኞቹ ምክንያቶች ናቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ የመንገድ ላይ ልመናን በብዛት መመልከት የተለመደ ከሆነ ሰነባብቷል። ወደ ጎዳና የሚወጣው የሰው ቁጥር ከአመት ወደ አመት ቁጥሩ እየጨመረ ችግሩን ከስረ መሰረቱ ለመቅረፍም አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል።

በርካታ ወጣቶች ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለሃገራት የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ነው ወደ መዲናይቱ አዲስ አበባ የሚጎርፉት። አብዛኛዎቹ ኑሮ እነሱ እንዳሰቡት ሳይሆን ይቀርና ውሎና አዳራቸው በጎዳና ይሆናል። ከማደሪያ ጀምሮ የዕለት ጉርሻን እንኳ ለማግኘት ይቸገራሉ አብዛኛዎቹ ወጣቶችም ረሃቡን እንግልቱን ለመርሳት ብርዱንም ለመከላከል ይረዳል በሚል በተለያዩ ሱሶች ይጠመዳሉ። ከወጡበት ለመመለስ በሃፍረትና በገንዘብ እጥረት ምክንያት ከመንገድ ይቀራሉ። የተወሰኑት ወዳጅ ዘመድ ያላቸው የክፍለሃገር ወጣቶች ደግሞ ኑሮን ለማሸነፍ በጥቃቅን ስራዎች እንደ ሎተሪ መሸጥና ሊስትሮ የመሳሰሉት ተባራሪ ስራዎች ላይ ይሰማራሉ።

በሊስትሮ ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶች
በሊስትሮ ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶች

ከአዲስ አበባ እስክንድር ፍሬው በመንገድ አግኝቶ ያነጋገራቸውና መስታወት አራጋው በስልክ ያገኘችውን አጭር ቃለመጠይቅ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።

ልመና፤ የጎዳና ኑሮ፣ የጎዳና ስራ በአዲስ አበባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG