በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የክረምቱ ዝናብ የጀመረ ቢሆንም የዘር እጥረትና የምግብ አቅርቦቱን ችግር ሊያራዝመው ይችላል ተባለ


የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ዶ/ር ዶርጅ ቢግረዋ
የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ዶ/ር ዶርጅ ቢግረዋ

በኢትዮጵያ የክረምቱ ዝናብ የጀመረ ቢሆንም የዘር እጥረት የምግብ አቅርቦቱን ችግር ሊያራዝመው እንደሚችል አንድ በአፍሪካ ግብርና ላይ የሚሠራ ድርጅት ኣስታወቀ።

የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት(አግራ) በመባል የሚታወቀው ይሀው ድርጅት እንዳለው የዘር አቅርቦት ጉዳይ የሚገባውን ያህል ትኩረት አልተሰጠውም።

የክረምቱ ዝናብ ጀምሯል የምግብ እጥረቱ ግን ሊቀጥል ይችላል ይላል የአፍሪካ አረንጓዴ አብዮት ጥምረት የተባለው ተቋም ፡ ድርጅቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው አብዛኛው ትኩረት በአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ላይ ሆኖ ቆይቷል። ብዙም የማናስተውለው የዘር ጉዳይ ግን ከባድ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል ብለዋል የድርጅቱ የምሥራቅና የደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ዶ/ር ዶርጅ ቢግረዋ።

የዝናቡ መምጣት ትርጉም ሊኖረው የሚችለው አርሶ አደሮቹ በቂ ዝግጅት ካደረጉ ብቻ እንደሆነ ኃላፊው ዛሬ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል አስረድተዋል።

ከድርጅቱ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ኃላፊ ጋር የተካሄደው ቃለ-ምልልስ ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ማዳመጥ ይችላሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በኢትዮጵያ የክረምቱ ዝናብ የጀመረ ቢሆንም የዘር እጥረትና የምግብ አቅርቦቱን ችግር ሊያራዝመው ይችላል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG