በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከመድረክ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ


ዶ/ር መረራ ጉዲና
ዶ/ር መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና
ዶ/ር መረራ ጉዲና

please wait

No media source currently available

0:00 0:28:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና ባለፈው ሣምንት መጨረሻ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኘው ናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዴሞክራሲ በሚባለው ተቋም ውስጥ ለተሰበሰቡ ታዳሚዎች ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

የዶ/ር መረራ ወረቀት ርዕስ፡- የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር አንድ እርምጃ ወደፊት፤ ሁለት እርምጃ ወደኋላ” የሚል ነው፡፡

ዶ/ር መረራ በዚህ ፅሁፋቸው ውስጥ ያለፉት 23 የኢሕአዴግ ዓመታት በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ፡…ያልተሣኩ ነበሩ…” ብለዋል፡፡

በ23ቱ ዓመታት መጀመሪያ ላይ የተነሡት ሥሉስ ቃላት - “ጎሣን መሠረት ያደረገ ፌደራላዊ ሥርዓት፤ ብዝኀ ፓርቲ ዴሞክራሲና የነፃ ገበያ ምጣኔ ኃብት - አልተከበሩም፤ የከሸፉ ቃላት ሆነዋል” ብለዋል፡፡

መጭውን ምርጫ አስመልክቶ ዶ/ር መረራ ሲናገሩ ተቃዋሚዎች በቀረው ጊዜ ተቃዋሚዎች እንዲተባበሩና ጥንካሬን እንዲፈጥሩ መክረዋል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ሙሉ ቃል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG