በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በታችኛው የኦሞ ወንዝ አካባቢ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ የመብት ረገጣ እየተካሄደ እንደሆነ የመብት ድርጅት ገለጸ


ኦሞ - ኢትዮጵያ
ኦሞ - ኢትዮጵያ

የሀገሬ ሰዎች መብት ተከራካሪው ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል አንደገለፀው በታችኛው ኦሞ ወንዝ ነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛ ነው።

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ኤልዛቤት ሀንተር እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግስት ነዋሪዎቹን ከሚኖሩባቸው ስፍራዎች ወደ ሌላ አካባቢዎች እያሰፈረ ይገኛል።

“ይህ ማለት ብዙዎቹ ነዋሪዎች ያለዉዴታቸው ከመኖሪያቸው አየተፈናቀሉ ነው። የመኖሪያ መንደራቸው ማንነታቸው ነው፤ ከብቶቻቸውን የሚያሰማሩበት፤ ለምሳሌ የከገሩ ማህበረሰብ ማር የሚቆርጡበትና አደን የሚሰማሩበት የተከበረ ባህላችሀዉን የሚተገብሩበት ቦታ ነው። እናም ይህ ሰፈራ ለጎሳዎቹ ከአቅማቸው በላይ ትልቅ ዱብዳ ሆኗል።”

የድምጽ ዘገባ በታችኛው ኦሞ ልማትና የማህበረሰብ መብት ዙሪያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ከሚመለከታቸው የጎሳው አለቆች ጋር በቀጥታ ስለ ሁኔታው ለመረዳት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ሀንተር ያስረዳሉ። ስለሁኔታው በአካባቢው የሚገኙ የውጭ ለጋሽ ሀገሮች ሰራተኞች በስፋት እንዳስረዷቸው አክለዋል። ይህ መረጃም በብርታንያ የመረጃ ነፃነት ህግን በመጠቀም የተገኘ ነው።

“በርግጥ የብርታንያ መንግስት ስለሁኔታው ያለዉን መረጃ ለሰርቫይቻል ለመስጠት ባይፈልግም ከአውሮፓ ህብረት መረጃውን ልናገኝ ችለናል።”

የጎሳው አባላት ከመኖሪያቸው ለመፈናቀል አለመፈለጋቸውን እንዳስረዷቸውና መረጃውንም ከማህበረሰቡ ማሰባሰባቸውን የመብት ተሟጋቿ ሀንተር ይገልጻሉ። ሁኔታው ከለጋሽ ሀገሮች መርሆዎች ጋር እንደሚጋጭም ያስረዳሉ።

“ጎሳዎቹ የሰፈሩባቸው ቦታዎች በተለይ አንዱ ለመኖሪያ ምቹ ኣይደለም። በአሁኑ ሰዓት ነዋሪዎቹ በወባና በተቅማጥ አየተሰቃዩ ነው፤ መንግስትም የሰፈራውን ቦታ ለቀው ወደ ሌላ ቦታ እንዳይሄዱ ከልክሏል።” ብለዋል ሀንተር

“ነዋሪዎቹን የማስፈር ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ቦታው ለከፍተኛ የሸንኮራ አገዳ ምርት ስራ ይውላል። የታቅደው የሸንኮራ አገዳ እርሻ ኩራዝ ይሰኛል፤ በጣም ሰፊ ነው።”

አቶ አለማየሁ ተገኑ የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር የኢትዮጵያ መንግስት ጎሳዎቹን ከቦታቸው ያለአግባብ አላፈናቀለም በማለት አስተባብለዋል።

አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፤ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር
አቶ ዓለማየሁ ተገኑ፤ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር

“ጎሳዎቹን ከመኖሪያ ቦታቸው አላፈናቀልንም። አሁንም በመኖሪያ ቦታቸው ላይ ይገኛሉ፤ መንግስትም እንደ ት/ቤት ያሉ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ግንባታዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። አንደማስበው ዘገባው ፍፁም ውሸት ነው።”

ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ አንዳሉት በወንዙ ዙሪያና አካባቢው የሚኖሩትን ነዋሪዎች ስለሚሰራው ግንባታ በተመለከተ በግልጽ መረጃ አድርሰዋል፤ በጋርም ሰርተዋል።

ለማህበረሰብ መብቶች መከበር የሚሰራው ድርጅት መርማሪ ሀንተር ከለጋሽ ሀገሮች ባገኙት መረጃ መሰረት፤ መንግስት ለእርሻ ስራ ወደ 500 ሺህ ሰራትኞችን ይፈልጋል። ወደ አካባቢው ለስራ የሚፈልሱት መጤ ሰራተኞች በአካባቢው ባህል፤ ወግና እምነት ላይ ያልተፈለገ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል።

አቶ አለማየሁ ተገኑ ይሄ አባባል ፈጽሞ አይዋጥላቸውም።

“ለህዝቦቻችን እንጠነቀቃለን፣ እናስባለን። ቅድሚያ የምናደርገውም ይህንኑ ነው። በህዝቦቿ ላይ ከመኖሪያቸው ማፈናቀልም ሆነ የሚገባቸውን ክብር መንሳት ኢትዮጵያዊ ባህላችን አይደለም። እቅዳችን ለህዝቦቻችን የተሻለ እድገትንና ጥቅምን ማምጣት ነው። እውነቱ ይህ ነው።”

አቶ እለማየሁ በአካባቢው እየተካሄደ ስላለው በአካል ተገኝቶ ለመመልከት ለሚፈልግ ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስት በሩ ክፍት አንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የመብት ድርጅቶች በኦሞ ወንዝ አካባቢ የሚገኙት ነዋሪዎች እውነቱን ለማውጣትና በይፋ ለማውጣት የደህንነት ስጋት እንዳለባቸው ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG