በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሙስሊሞቹ ጥያቄዎች መሪዎች ቤቶች በፖሊስ ተፈተሹ


የታሠሩ የኮሚቴው አባላት እንዳሉም ተሰምቷል፡፡

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

ማምሻውን በደረሰን ዜና ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ ጀምሮ የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ጥያቄ ለመንግሥት እንዲያቀርብ የተሰየመው ኮሚቴ አባላት መኖሪያ ቤቶች በፖሊስ ተከበው እየተፈተሹ መሆኑን ከኮሚቴው አባላት አንዱ አቶ አህመዲን ጀበል በስልክ ገልፀውልናል። ስለ እርምጃው እስካሁን ከኢትዮጵያ ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ የለም።

ሆኖም አቶ አህመዲን እንደገለፁልን ከፍተኛ የእስልምና እውቀት ያላቸው ሦስት አዛውንት ጭምር በጠቅላላው የሃያ አራት ሰዎች ቤቶች ተፈትሿል።

የኮሚቴው አባላት ስለዚህ የሚያውቁት ካለ ተጠይቀው አቶ አህመዲን ለቪኦኤ በስፋት አብራርተዋል፡፡

በአወሊያ ተቋም ዙሪያ ህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎቹን ለመንግሥት የሚያቀርብ አሥራ ሰባት አባላት ያሉት ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዙት የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG