በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አበባ ሙስሊሞች በአንዋር መስጊድ ተቃውሞ አካሄዱ


“ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሮመዳንን የተቀበለው እያዘነ ነው”

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

በዓርቡ የአንዋር መስጊድ የሙስሊሞች ፀሎትና ተቃውሞ ላይ የተገኙ ስማቸው እንዳንገልጽ የጠየቁን አንድ የሙስሊሙ የመብት እንቅስቃሴ ተሣታፊ “ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ሮመዳንን የተቀበለው እያዘነ ነው” ብለዋል።

“የሙስሊሙ ማኅበረሰብ የሮመዳንን ፆም እያዘነ የተቀበለው እጅግ የሚወዳቸው የሃይማኖት አስተማሪዎቹ ያለ አግባብ ቤታቸው እየተበረበረና እየተሣደዱ መሆኑን እያሰበ በመሆኑ ነው” ብለዋል።

ትላንትና ማታ አሥራ ሰባቱ የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ዳአኢዎችና ዑስታዞች ቤታቸው እንዲበረበርና ባሉበት እንዲያዙ ማዘዣ መውጣቱን በመስማቱ ከአምስት መቶ ሺህ በላይ የሚሆን ምዕመን በተቃውሞው ላይ መገኘቱን ለቪኦኤ ገልፀዋል። ይህ ሁኔታ “ዛሬን የተለየ ያደርገዋል”ም ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ብሉምበርግ ጋዜጣ ዛሬ ባወጣው ፅሁፍ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ መሥሪያ ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን “የታሠሩት አመፅ ቀስቃሾች ናቸው፤ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ህገመንግሥቱን መናድ ይፈልጋሉ” ማለታቸውን ጠቅሷል።

ዝርዝሩን ከዓርቡ ተቃውሞ ተሣታፊ ጋር ትዝታ በላቸው ከደረገችው ቃለምልልስ ያድምጡ።

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )


XS
SM
MD
LG