በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክረምቱ ዝናብ ለሳምንታት ከተለመደው በላይ ተጠናክሮ ስለሚቀጥል ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጠ


ሰሞኑን ጎርፍና የመሬት መናድ በኢትዮጵያ አደጋና ችግሮችን እያስከተለ ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች እስከአሁን ወደ አርባ የሚጠጋ ሰው ሕይወት መጠየቃቸውን፣ በተለያዩ አካባቢዎች መፈናቀልና የንብረት ውድመት ማስከተላቸውን በተለያዩ ዘገባዎቻችን እያቀረብን እንገኛለን፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዲሬክተር አቶ ኪዳኔ አሰፋ የዚህ ክረምት የዝናብ ሁኔታ ከመደኛው ከፍ ያለ መሆኑን ገልፀው ሕዝቡ ከባድ ዝናብና ጎርፍ፣ በገደላማ አካባቢ የሚኖረውም ሰው የመሬት መንሸራተት እንደሚኖር አውቆ ሕይወቱን፣ ቤተሰቡን፣ እንስሣቱንና ንብረቱን ከአደጋ መጠበቅ እንዲችል በእንቅስቃሴው ሁሉ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሣስበዋል፡፡

ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የዕለት፣ የሦስት ቀናት የአሥር ቀናት ትንበያዎችን እያዘጋጀ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መረጃም እንደሚበትን ያሣወቁት የኤጀንሲው ዋና ዲሬክተር እንደግብርናና ውኃ ኃብትን ጨምሮ ከበርካታ መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር በቅርበት እንደሚሠራ መረጃም እንደሚለዋወጥ ጠቁመዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በማከልም ምንም እንኳ እንኳ ኤጀንሲያቸው ስፋት ያላቸውንና ተአማኒነታቸውም ከፍተኛ የሆነ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ቢሰጥም በአካባቢ የተወሰኑ ልዩ ትንበያዎችን ለማድረግ ግን የአቅም ውሱንነት እንዳለው ገልፀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG