በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፓርላማ አባል የግቤ ግድብ ግንባታ እንዲቆም ጠየቁ


ድንበር ጥሰው የኬንያ ክልል ውስጥ ሰፍረዋል የተባሉትን የደቡብ ኢትዮጵያ የሜሪሌ ጎሣ አባላት የኬንያ ሠራዊት እንዲያስወጣ መታዘዙ በ allafrica.com ዌብሣይት ተዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ሜሪሌዎችን በሠላም ወደመጡበት እንዲመልስ አልያ በኃይል እንዲወጡ እንደሚደረግ የኬንያ መንግሥት ማሣወቁም በዚሁ allafrica.com ዌብሣይት ተጠቅሷል።

ትዝታ በላቸው ያነጋገረቻቸው አንድ የኬንያ ፓርላማ አባል ግን የጎሣ አባላቱ በአካባቢው ድርቅና የግጦሽ መሬት መመናመን የተጎዱ መሆናቸውን በመጠቆም ጉዳዩ ዘላቂ መፍትሄ ይሻል ይላሉ።

በደቡብ ኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አቅራቢያ የሚኖሩ አርብቶ አደር ጎሣዎች በግጦሽ መሬትና ለከብቶቻቸው ውኃ ፍለጋ በሚያደርጉት ድንበር ዘለል እንቅስቃሴ ግጭቶች የተለመዱ ናቸው። ሜሪሌ ወይም ዳሰነች በመባል የሚታወቁት የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔረሰብ አባላት ከሁለት ሣምንታት በፊት ከኬንያ ቱርካና ጎሣዎች ጋር በተካሄደ ግጭት አርባ ሰዎች እንደገደሉ የኬንያ መንግሥት ገልጿል።

አሁን ደግሞ ቁጥራቸው 2 ሺህ 500 የሚሆኑ የታጠቁ የሜሪሌ ጎሣ አባላት ቱርካና ሐይቅ አካባቢ የሚኖሩ የቱርካና እና ሌሎች ማኅበረሰቦችን በመግፋት 14 ኪሎ ሜትሮች ዘልቀው ኬንያ ውስጥ ሠፍረዋል ተብሏል።

<allafrica.com> እንደዘገበው የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ወደመጡበት እንዲመልስም የኬንያ መንግሥት ጠይቋል። የኬንያ ሠራዊት እነዚህን ሰዎች እንዲያስወጣ ወደ ድንበር ተልኳል።

የኬንያ ማዕከላዊ ቱርካና ግዛት ምክር ቤት ተወካይ ሚስተር ኢክዌ ኢቱሩ ሁኔታውን እንዲያብራሩልን ጠይቀናል።

በኬንያ ፓርላማ የኬንያ ምክር ቤት አባል ሚስተር ኢክዌ ኢቱሩ የኬንያ ፕሬዚደንት ምዋዪ ኪባኪና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ባለፈው ሣምንት በድንበሩ ህዝቦችና የተፈጠረው ግጭት ዙሪያ መወያየታቸው የጉዳዩን አሣሣቢነትና ሁለቱን አገሮች መፍትሄ እንደሚሻ ጠቋሚ ነው ይላሉ።

በመጨረሻም የሁለቱ መንግሥታት የህይወት ደህንነትና የንብረት ጥበቃን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፣ በጋራ ድንበሮቻቸው አካባቢ ፀጥታን የማስጠበቅ፣ ሜሪሌዎችን በሰላም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማረጋገጥና የህዝቡን ችግር ለማቅለል አስፈላጊዉን መሠረተ ልማት መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ሙሉውን ዘገባ ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG