በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያና የኬንያ ጦሮች በአልሻባብ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈቱ


የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ /ፎቶ ፋይል - ከኮምፕዩተር ስክሪን ላይ የተወሰደ/
የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ /ፎቶ ፋይል - ከኮምፕዩተር ስክሪን ላይ የተወሰደ/

ሶማሊያ ግድጅ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች ጌዶ እና ቤይ በሚባሉት ሁለት የሶማሊያ ክፍለ ሀገሮች በጽንፈኛ የሁከትና የሽብር ቡድን አልሸባብ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈቱ፡፡

የኬንያ ወታደር በሶማሊያ /ፎቶ ፋይል/
የኬንያ ወታደር በሶማሊያ /ፎቶ ፋይል/

ሶማሊያ ግድጅ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያና የኬንያ ወታደሮች ጌዶ እና ቤይ በሚባሉት ሁለት የሶማሊያ ክፍለ ሀገሮች በጽንፈኛ የሁከትና የሽብር ቡድን አልሸባብ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈቱ፡፡

በሶማሊያ ያለው የአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ አሚሶም ባወጣው መግለጫ የጁባ መተላለፊያ ዘመቻ (ኦፐሬሽን ጁባ ኮሪዶር) ተብሎ የተሰየመው ጥቃት ዓላማ ሽብርተኛውን ቡድን ከገጠሩ አካባቢዎች ለመደምሰስ ነው ብሏል።

ከትናንት በስቲያ ዓርብ በጌዶ ክፍለ ግዛት ፋሃዱን ከተማ ከሚገኘው የኬንያ ወታደሮች ሠፈር የተከፈተው የመጀመሪያው ጥቃት በእማኞች መሰረት በክፍለ ሀገሩ የመጨረሻዋ የኣልሰብባ ጠንካራ ይዞታ ባርዴሬ ሃምሣ ኪ.ሜ ላይ የምትገኝ ታራኮ ወረዳ ደርሷል።

ትናንት ዓርብ ደግሞ የኢትዮጵያና የሶማሊያ መንግሥት ወታደሮች ባይ ክፍለ ሃገር ከቃንሳዴሬ የተከፈተ ሲሆን ከባርዴሬ ስድሣ አምስት ኪ.ሜ ርቀት ተቃርቧል ሲሉ አንድ የሶማሊያ ጦር ኃይል ቃል አቀባይ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኃይሎች የአልሻባብ ጊዜያዊ ዋና ጣቢያ ዲንሶርንም ያጠቃሉ ተብሎ የተጠበቀ ሲሆን ሆኖም ባይዶዋ ያለ የቪኦኤ ዘጋቢ እንዳለው ከሆነ አልሸባቦቹ በተወሰነ ደረጃ መክተው እየተዋጉ ናቸው።

ዛሬ ወደዲንሶር ይገፉ የነበሩትን ወታደሮች ዒላማ ያደረገ መኪና ሙሉ ቦምብ ፈንድቶ ሁለት የሶማሊያ ወታደሮችን ሲገድል ከዲንሶር አርባ ኪ.ሜ ርቀት ላይ ውጊያ መካሄዱን ዘገባው ጠቁሟል።

የሶማሊያው ጦር ቃል አቀባይ በአየር ኃይልም እያጠቃን ነው ማለታቸው ተጠቅሷል።

ይህ አዲሱ ጥቃት ዋና ዋና የአቅርቦት መሥመሮችን አፅድቶ ለህዝቡ ሰብዓዊ ረድኤት እንዲደርስ ማመቻቸት እና አልሸባብን ከተጠቀሱት አካባቢዎች በማጥፋት ፌዴራሉ መንግሥት ሙሉ በሙሉ እንዲቆጣጠር ማድረግ ነው ሲሉ የአሚሶም ምክትል አዛዥ ሞሃመዲሻ ዜይኑ ባወጡት መግለጫ አስረድተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ካዘመተች አንስቶ የአልሸባብ ገዳይ ጥቃቶች ዒላማ የሆነችውን የአባታቸው የትውልድ ሃገር የሆነችውን ኬንያን ይጎበኙና በማስከተል ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ።

XS
SM
MD
LG