በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ለስኳር ምርት ሰዉን ያፈናቅላል ሲል ሂ.ራ.ዋ ከሠሠ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ


በታችኛው ኦሞ 200 ሰው ያለበት 245 ሺህ ሄክታር መሬት ለስኳር ልማት ይውላል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ለስኳር ምርት ሲል ለሸንኮራ አገዳ እርሻ ለማዋል በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎችን በግድ እያነሣ ነው ሲል ዋና መሥሪያ ቤቱ ለንደን የሚገኘው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የማንሣትና የማስፈሩ ሥራ እየተከናወነ ያለው በሰዎቹ በራሣቸው ፍቃድ ነው ይላል፡፡

“በመንግሥት ካርታዎች ላይ እንደሠፈረው ወደ 245 ሺህ ሄክታር ከሚሆን መሬት ላይ ሰዉ ተነስቶ ለስኳር ምርት የሚውል ተክል እርሻ ይሆናል፡፡ በአካባቢው ወደ ሁለት መቶ ሺህ የሚሆን ሰው እንደሚኖር ጥናቶች ያሣያሉ፡፡ በመሆኑም በታችኛው ኦሞ ሸለቆ ሁለት መቶ ሺህ የሚሆን ሰው ተጋላጭ ነው፡፡ በወሰን አካባቢ በቱርካና ሐይቅ ደግሞ ሌላ ሦስት መቶ ሺህ ሰው ሕይወቱን በቱርካና አካባቢ ባለው መሬት ላይ የመሠረተ ነው፡፡” ብለዋል በታችኛው ኦሞ ሸለቆ ጉብኝት አድርገው የተመለሱት የሂዩማን ሣይትስ ዋች ባልደረባ ፌሊክስ ሆርን፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት “የተዛባ” እና “የተጋነነ” ነው ሲሉ ማስተባበያ የሰጡት የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምዖን ልማቱ እየተካሄደ ያለው “ለነባሮቹ ሕዝቦች የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ፣ ታሪካዊና ባሕላዊ ሃብቶች ተጠብቀው፣ ለሁሉም ኢትያጵያዊያን ጥቅም እንዲሰጥ ነው” ብለዋል፡፡

የግብርና ልማት ለሚያካሂዱ ኩባንያዎች አራት ሚሊየን ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ወር ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከማጫወቻዎቹ አንደኛውን ብቻ አስቀርተው የቀሩትን ያቁሟቸው፡፡)


XS
SM
MD
LG