በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በቤኒሻንጉል የአባይ ወንዝን ገድባ የጣና ሀይቅን ሁለት እጥፍ የሚሆን ውሃ ልታከማች ነው


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ በሱዳን

ድንበር አጠገብ ልትገንባው ያቀደችው 5200 ሜጋዋት የሚያፈልቅ

የኤለክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ እንዳይሰራ፣ በመጣር ላይ ባሉት ወገኖች

ላይ፣ ከባድ ትግል ጀምረዋል።

ግዙፉ ውጥን ኢትዮጵያ፣ የኤለክትሪክ ሃይል ወደ ውጭ በመላክ፣ እጅግ

አስፈላጊ የሆነውን፣ የውጭ ገቢ እንድታገኛ ያስችላታል ይላሉ ጠቅላይ

ሚኒስትሩ። ይሁንና በአብዛኛው ከግብጽና ከአከባቢ ጥራት ተከራካር ቡድኖች

በቀረበው ተቃውሞ ምክንያት፣ ኢትዮጵያ የገንዘብ ምንጭ ደርቆባታል።

አቶ መለስ በአለም አቀፉ የሀይድሮፖወር ጉባኤ መክፈቻ ላይ፣ ባደረጉት

ንግግር፣ $4.8 ቢልዮን ዶላር የሚያወጣው ውጥን፣ በሀገሪቱ ወጪም ቢሆን

መሰራቱ እንደማይቀር አስታውቀዋል።

“በአላማችን ፍትሃዊንትና በእምነታችን ጥንካሬ ስለምንተማመን የመብራት

ሃይሉ ውጥናችን ድህነትን በማጥፋት ረገድ ሚና እንደሚኖረው ስለምናምን

ያለንን ጥንካሬ ሁሉና ሳንቲም ሳይቀር ያለንን ገንዘብ ቆጥበን በመጠቀም

እቅዱን እናጠናቅቃለን” ብለዋል አቶ መለስ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጥኑ ገንዘብ ላለማቅረብ የወሰኑትን ወገኖች፣ ፍትህ

የጎደለው ተግባር በማለት ነቅፈዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትርሩ ግብጽና ሱዳን ከግድቡ እንደሚጠቀሙ ግንዛቤ ያገኛሉ የሚል እምነት አላቸው።

በኢትዮጵያ የግብጽ አምባሳደር፣ ታሪቅ ጎኒም ለአሜሪካ ድምጽ ሬደዮ

ሲናገሩ፣ ሀገራቸው የአባይ ወንዝ ውሀ ድርሻን በሚመለከት፣ ላለው ጠብ፣

ጥሞናዊ መፍትሄ ለማግኘት፣ ለድርድር ክፍት ናት ብለዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG