በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ምንም ያገኘነው ርዳታ የለም”- ሰባት ቤተሰቦቹን ያጣ ወጣት


ስዩም በየነ ይባላል ሰባት ቤተሰቦቹን አጥቷል በዛሬ ዕለት ለለቅሶ በተቀመጠበት ተገኝቶ ነው የተነሳው። የአንድ ወንድሙን አስክሬን በመጠበቅ ላይ ናቸው።
ስዩም በየነ ይባላል ሰባት ቤተሰቦቹን አጥቷል በዛሬ ዕለት ለለቅሶ በተቀመጠበት ተገኝቶ ነው የተነሳው። የአንድ ወንድሙን አስክሬን በመጠበቅ ላይ ናቸው።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ነገሪ ከዚህ አደጋ በህይወት ተርፈው በተለያየ ቦታ የሚገኙ ሰዎችን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሆነና በዘላቂነት መልሶ እንዲቋቋሙ እንደሚደረግ ገልፀውልናል።

ስዩም በየነ ይባላል፡ የ17 ዓመት ወጣትና የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነው። ቆሼ እየተባለ በሚተራው ቦታ ተወልዶ ማደጉን ይናገራል። የሚኖሩበት ቤት መካከለኛ የሚባል እንደሆነና በግቢያቸው ውስጥም ተከራዮች እንደነበሩ ይናገራል።ዩም ቅዳሜ ምሽት በቤታቸው ውስጥ የደረሰውን አደጋ ሲያስረዳ፤ በእነርሱ ቤት ውስጥ አራስ የወንድሙን ሚስት ሊጠይቁ የመጡ አክስቱና ስድስት ቤተሰቦቹ በአጠቃላይ በደጋው ሕይወታቸውን አጥተዋል። በግቢያቸው ውስጥ ከነበሩ ተከራዮችም ዐስር ሰዎች በአደጋው ሕይወታቸው ተፍቷል። በአጠቃላይ ከእነርሱ ግቢ ውስጥ 17 ሰው ሞቷል።

የእርሱ የወንድም ልጅ እና የተወሰኑት የተከራይ አስክሬን እየተፈለገ እንደሆነ ነግሮናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ፍለጋው እንደቀጠለና የሟቾች ቁጥር 113 መድረሱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ከደረሰ በኋላ ለተጎዱት ሰዎች ፈጣን ርብርብ አልተደረገም በዚህም ምክኒያት ሊተርፉ ይችሉ የነበሩ ሰዎች ሕይወት አልፏል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አነጋግረናል።

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

“ምንም ያገኘነው ርዳታ የለም”- ሰባት ቤተሰቦቹን ያጣ ወጣት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:13 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG