በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የ274 ቢሊዮን ብር አመታዊ በጀት ፀደቀ


የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አብዱአልዚዝ አህመድ
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አብዱአልዚዝ አህመድ

ለ2009 ዓ.ም የበጀት ዓመት 274 ቢሊዮን ብር መፅደቁን የኢትዮጵያ የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

2009. የተመደበው 274 ቢሊዮን ብር የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ካለፉት ዓመታት የተሻለ እንጂ ያነሰ አለመሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ድርቁ በበጀቱ ላይ ተፅዕኖ አለማሣደሩን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ሃጂ ኢብሳ ገልፀዋል፡፡

2009 .በጀት ረቂት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ያቀረቡትት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር አብዱአልዚዝ አህመድ ናቸው።

ከተጠየቀው የ274 ቢሊዮን ብር በጀት ከ65 በመቶ በላይ የሚሆነው ድህነት ተኮር በሆኑ ዘርፎች ላይ እንደሚውልም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

በጀቱን በተመለከተ ለአሜሪካ ድምፅ ተጨማሪ ማብራርያ ከሰጡት የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ሃጂ ኢብሳ ጋር የተካሄደ ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

በኢትዮጵያ የ274 ቢሊዮን ብር አመታዊ በጀት ፀደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG