በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብፅ ከስብሰባ ቀረች፤ ደቡብ ሱዳን አባል ሆነች


ቢሾፍቱ
ቢሾፍቱ


የአባይ / ናይል ተፋሰስ
የአባይ / ናይል ተፋሰስ

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ናይል ቤዚን ኢኒሽየቲቭ እየባለ የሚጠራው የናይል ተፋሰስ ጅማሮ ባለፈው ሣምንት አዲስ አበባ ላይ ባካሄደው የምሥራቅ ናይል ሃገሮች ስብሰባ ላይ ግብፅ እንደማትሣተፍ በፅሁፍ አሣውቃ መቅረቷ ተገልጿል፡፡

የምሥራቅ ናይል ንዑስ ተፋሰስ መርኃግብር ሚኒስትሮች ምክር ቤት ደቡብ ሱዳንን አባል አድርጎ ተቀብሏታል፡፡

የግብፅ የመስኖ ሚኒስቴር ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ መሠረት ግብፅ ባለፈው ሣምንት ከጥር 21 እስከ ጥር 23 / 2006 ዓ.ም ቢሾፍቱ ላይ በተካሄደው የምሥራቅ ናይል ንዑስ ተፋሰስ የድርጊት መርኃግብር አባል ሃገሮች ስብሰባ ላይ እንደማትገፀ አስታውቃ ቀርታለች፡፡

ሞሐመድ አብዱል ሙታሊብ - የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር
ሞሐመድ አብዱል ሙታሊብ - የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር
የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብዱል ሙታሊብ ዩም-7 ለሚባል የሃገራቸው ጋዜጣ በሰጡት ቃል ግብፅ የናይል ተፋሰስ የትብብር ጅማሮ ወይም የናይል ቤዚን ኢኒሽየቲቭን የስብሰባ ጥሪ ውድቅ አድርጋ የቀረችው ሃገሪቱ ለረዥም ዓመታት ይዛው የቆየችው በዓመት የ84 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ፍሰት ካለው የናይል ውኃ የ55.5 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትሩ ዓመታዊ ፍሰት የተጠቃሚነት መብት እስካልተረጋገጠላት በማንኛውም ሁኔታ ላለመተባበር አሳውቃ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ግብፅ ኢንተቤ-ዩጋንዳ ላይ የተፈረመውን የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትም እአአ ከ2010 ዓ.ም አንስቶ ስትቃወም መቆየቷን ሚኒስትሩ መግለፃቸውን ዩም-7 እና ዘ ካይሮ ፖስት ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡

አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር
አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር
ግብፅ በደብዳቤ ባሳወቀችው አቋሟና ኅዳሴ ግድብን ጨምሮ በሌሎችም የተፋሰሱ ጉዳይ በሆኑ ነጥቦችን ላይ በኢትዮጵያ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና የወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG