በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብፅ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን መጎብኘት ይፈልጋሉ


አዲሱ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ኢትዮጵያን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቃቸው ተገለፀ፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:10:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


አዲሱ የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደል-ፋታህ ኤል-ሲሲ ኢትዮጵያን የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ማሳወቃቸው ተገለፀ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ፍላጎታቸውን የገለፁት በሹመታቸው በዓል ላይ ከተገኙት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር በተወያዩበት ወቅት መሆኑን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በፕሬዚዳንት ኤል-ሲሲ የሹመት በዓል ላይ እንዲገኝ ለኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ መድረሱን የገለፁት አምባሣደር ዲና ኢትዮጵያ የውጭ ሚኒስትሯን መላኳን አስታውቀዋል፡፡
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
ለምን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ፕሬዚዳንቱ አልሄዱም ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ አምባሣደር ዲና ሲመልሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ቢሆን ኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ መገኘቷን ገልፀው ሁኔታው በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያለውን ግንኙነት በምንም ሁኔታ እንደማይመለከት፣ ከሌሎች ሃገሮችም በተመሣሣይ ደረጃ ያሉ ልዑካንን መገኘታቸውን አስረድተዋል፡፡

ምንም እንኳ ከፈርዖን ዘመን ጀምሮ በአባይ ላይ የተለየ አመለካከት ያላቸው የግብፃዊያንን ሃሣብ ድንገት ይለወጣል ተብሎ የማይጠበቅ ቢሆንም አሁን ወደ ሥልጣኑ ከዘለቁት መሪዎች የተሻለ አስተሳሰብ እየተሰማ መሆኑን አምባሣደር ዲና አመልክተው ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ ኤል-ሲሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ተገናኝተው በተነጋገሩበት ወቅትም በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መካከል የነበረውና የግብፅ ተደራዳሪዎች ኻርቱም ላይ ረግጠው በመውጣታቸው ምክንያት የተቋረጠው የሦስትዮሽ ምክክር እንዲቀጥል መስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡

አምባሣደር ዲና በመቀጠልም “የሁለቱን ሃገሮች ግንኙነቶችና በመሪዎች ደረጃ የሚደረጉ ጉብኝቶችን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ለንግግርና ለመልካም ግንኙነት ዝግጁነቷን እንደገለፀች ነው” ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ የሰጡትን ቃለምልልስ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG