በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ. ለረሀብ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ


ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ
ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ

የተ.መ.ድ. የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ (UNICEF) ኢትዮጵያ ውስጥ ሊደርስ ይችላል ለተባለው ረሀብ፣ ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ።

በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ከ 8.2 ሚልዮን ወደ 10.2 ሚልዮን ከፍ ማለቱን መንግስት አታወቀ። ይህም ሆኖ እስካሁን ባለው ጊዜ ከለጋሾች እየተገኘ ያለው ድጋፍ አነስተኛ መሆኑን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሜቴ ጸሀፊ አቶ ምትኩ ካሳ ተናግረዋል።

ድርቁን ባለፉት 50 አመታታ ውስጥ በሀገሪቱ ከተከሰቱት ሁሉ አስከፊ ሲል የገለጸው የህጻናት አድን ድርጅት ሴቭ ዘ ችልድረን(Save The Children) በበኩሉ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል። ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው ዘገባውን አቅርቦታል ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የተ.መ.ድ. ኢትዮጵያ ውስጥ ሊደርስ ይችላል ለተባለው ረሀብ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:48 0:00

የኢትዮጵያ ገበሬዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:58 0:00

ዩኒሴፍ እንደተነበየው፣ አፋጣኝ ምላሽ ከተሰጠ፣ ረሀቡ ደርሶ በቀን ሊወጣ የሚችለውን ገንዘብ በ$8 ሚልዮን (Million) ማዳን ይቻላል።

ከEl-Nino ጋር የተያያዘ ብሩቱ ድርቅ ባስከተለው በዚህ የኢትዮጵያው አስከፊ ረሀብ፣ ከወር በኋላ በሚጀምረው በአአ 2016 ዓም፣ 5.75 ሚልዮን (Million) ህፃናትን ጨምሮ፣ 10.1 ሚልዮን (Million) ሕዝብ፣ ለከፍተኛ የመግብ እጥት ሊጋለጥ እንደሚችል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በዛሬው ዕለት አስታውቋል።

ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ፣ 57% ህፃናት ናቸው።

በዚሁ የአውሮፓውያኑ 2016 ዓም፣ ወደ 400,000 ህፃናት፣ ለተመጣጣኝ መግብ እጥረት የተጋለጡ መሆናቸውም ተመዝግቧል።

እናም ፓሪስ ውስጥ በዚህ ሳምንት በአየር ንብረት ጉባዔ የተሰበሰቡት የዓለም መሪዎች፣ ለዚህ በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ለተከሰተ አስከፊ ድርቅ፣ አፋጣኝ መልስ ሊሰጡ ይገባል ሲሉ፣ በኢትዮጵያ የሴቭ ዘ ችልድረን(Save The Children) ጆን ግራም (John Graham) አስጠንቅቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ቀውሱን ለመግታት ይቻል ዘንድ ያልተጠበቀ የ$192 million ወጪ ያደረገ ሲሆን፣ የተባባሰ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ግን ዓለማቀፉ ማኅበረሰብ አጣዳፊ ምላሽ መስጠት እንዳለበት ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG