በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በኤል-ኒኞ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ቢያበቃም ተፅዕኖው እንደሚቀጥል ተገለጸ


የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ
የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ

በኤል-ኒኞ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ቢያበቃም አሉታዊ ተፅዕኖው እንደሚቀጥል የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አስታወቁ።ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስታወቁት እርዳት የሚቀርብለት ህብረተሰብ ከዚህ ማእቀብ ሊወጣ የሚችለው ምርት ከተሰበሰበ በኃላ ነው።

የኤል-ኒኞ ወቅት አብቅቷል የክረምቱ ዝናብም ቀጥሏል።ያለፈው አመት በዚህ ሰዓት ግን ሁኔታው እንዲህ አልነበረም።ወቅቱን ጠብቀው ለሥራ ለተገኙት የዚች አገር አርሶ አደሮች ያሰቡት ዝናብ አልመጣም የለመዱት ሁኔታም አልቀጠለም። 10.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ዚጎች የእርዳታ ጥገና ሆነው ቆይተዋል። እንሆ ዘንድሮ ግን ዝናብ እየበዛ ነው። በልግ አብቃይ በሆኑ አከባቢዎች ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ዝናብ ዘንቧል ጎርፍም አስከትሏል።መህር አብቃይ ለሚባሉት ደግሞ እንሆ ክረምቱ ዝናብ የያዘ ይመስላል።

በድርቁ ምክንያት የምግብ እጥረት ያጋጠማቸው ወገኖች ግን እንዲህ በአንድ ጊዜ ከተረጂነት ሊወጡ ኣይችሉም የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ለአሜሪካ ድምፅ እንዳብራሩት ድርቁ ቢያበቃም ተፅዕኖው በተለይም ምርት እስከሚሰበሰብ ይቀጥላል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኢትዮጵያ በኤል-ኒኞ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ ቢያበቃም ተፅዕኖው እንደሚቀጥል ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:12 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG