በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዶሎ ኦዶ የፖሊዮ ጥርጣሬ


ዓርብ፤ ጥር 18 2012 ሃገርአቀፍ ፀረ-ፖሊዮ ዘመቻ ይጀመራል፡፡

በምሥራቅ ኢትዮጵያ የዶሎ ኦዶ የስደተኞች መጠለያ ሠፈርና በአካባቢው የፖሊዮ መቀስቀስ ጥርጣሬ አለ፡፡

በዶሎ ኦዶ አካባቢ ካሉት የስደተኞች መጠለያ ሠፈሮች በአንደኛው ላይ ሁለት፣ እንዲሁም ከአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ ሦስት ሰዎች ሕክምና ፍለጋ ወደ ጤና ተቋም ሲሄዱ የፖሊዮ ችግር ሣይሆን አይቀርም ብለው ሃኪሞቹ የገመቱ መሆኑን የዩኤንኤችሲአር የኢትዮጵያ ቢሮ የሕዝብ መረጃ ክፍል ኃላፊ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

የቫይረሱን ዓይነት በሥፍራው መለየት ባለመቻሉም ናሙናው ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ላብራቶሪ ተልኮ ውጤቱን እየጠበቁ መሆኑን ቃልአቀባዩ አመልክተዋል፡፡

ውጤቱ እንደታወቀም የተጠረጠረው የፖሊዮ ችግር እርግጠኛ ሆኖ ከተገኘ ክትባት ማግኘት ለሚገባው የዕድሜ ክልል ክትባት ለመስጠት እና ለሕሙማኑም የሚገባውን ሕክምና ለመጀመር የስደተኞች ኮሚሽነሩና አጋሮቹ ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ክሱት ገልፀዋል፡፡

ዐርብ፣ ጥር 18 / 2012 ዓ.ም ቀን ሃገር አቀፍ ፀረ-ፖሊዮ ዘመቻ እንደሚጀመርና በክትባቱ ውስጥም የስደተኞቹ ካምፖችም መካተታቸውን አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር አስረድተዋል፡፡

ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG