በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ለመርዳት ወደ ሃገሪቱ የተላከው የዩናይትድ ስቴስ ቡድን $530 ሚልዮን ዶላር እንተመደበለት ተገለጸ


ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት (USAID) መሥሪያ ቤት
ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት (USAID) መሥሪያ ቤት

የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት (USAID) በኢትዮጵያ የተከሰተውን ከባድ ለማቃለል በሚደረገው ጥረት የሚረዳ ቡድን ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደላከ የአገልግሎቱ ስራ አስኪያጅ ጌል ስሚት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ኤል ኒኖ በተባለው የአየር ለውጥ ምክንያት የተከሰተው ድርቅ የከፋ ሁኔታ ከማስከተሉ በፊት ለመቆጣጠር የሚቻልበት ስራ እንደተጀመረ ኢትዮጵያ የገባው ቡዱን መሪ ጆናታን አንደርሰን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ገልጸዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ቁም እንስሳት ግን እነደሞቱ አንደርሰን ጠቁመዋል።

ዳርት (DART) በሚል የእንግሊዘኛ አሕጽሮት የሚታወቀው በውጭ ሀገራት የተከሰቱ ቀውሶችን በማስወገድ ተግባር የሚረዳ የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት ክፍል የከፋ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት የድርቁን ሁኔታ ለመቆጣጠር ወደ ኢትዮጵያ እንደተላከ የቡድኑ ምክትል ሃላፊ ጆናተን አንደርሰን ገልጸዋል።

ወደ ኢትዮጵያ የተላኩት ሰዎች 14 ሲሆኑ የቡድኑ አባላት ቁጥር እንዳስፈላጊነቱ ሊጨምርና ሊቀንስ እንደሚችል አክለው ገልጸዋል። የቡድኑ አባላት በሰብአዊ ረድኤት የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው ሰዎች፣ የሎጂስቲክስ ድጋፍ የሚሰጡ ቴክኒካዊ አምካሪዎችና የቀንድ ከብት ባለሙያዎች እንደሚገኙባቸው ጆናታን አንደርሰን ተናግረዋል።

ጆናታን አንደርሰን ቡድኑ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ ከገባ ወዲህ ስላከናወናዋቸው ተግባሮች ገልጸዋል።

“ጥናት አካሂደናል። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን የገጠማት ድርቅ በአምሳ አመታት ውስጥ ባልታየ አይነት የከፋ ነው። ድርቁ የተከሰተው ትግራይን፣ አፋርን፣ የአማራ ክልልን የደቡብ

ህዝቦችን፣ የሶማሊ ክልልንና ኦሮሚያን ባካተቱ ስድስት ክልሎች ነው። ብዙ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን ለማያት ችለናል። የምግብና የሚጠጣ ውሀ እጥረት አለ። ከመኖርያ መፈነቀልም እያስከተለ ነው።”

በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅን በሚመለከት እስካሁን ባለው ጊዜ በተደረገው ጥናት መሰረት ሰዎች በድርቁ ምክንያት የተጎዱ ቢሆንም የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን የሚያሳይ ምልክት እንደሌለ የገለጹት ጆናታን አንደርሰን እስካሁን ባለው ጊዜ የበዛ እርዳታ ያቀረበው የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንደሆነ ጠቁመዋል።

በውጭ ሀገራት የተከሰቱ ቀውሶችን በማስወገድ ተግባር የሚረዳ የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት ክፍል (DART) በኢትዮጵያ ለሚያካሄደው ስራ ከ $530 ሚልዮን ዶላር በላይ እንደተመደበለት አንደርሰን ገልጸዋል። ይህ የተመደበው ገንዘብም ቡድኑ ከመላኩ በፊት ሲሰራበት እንደቆየ የዚህ ቡድን ሀላፊነትም የተጀረውን ስራ ማቀላጠፍ መሆኑን አንደርሰን ጨምረው ገልጸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ባለው ጊዜ የለገሰችው 400 ሚልዮን የወጣበት የምግብ ረድኤት ለአራት ሚልዮን ተረጂዎች ተከፋፍሏል። በበቂ ምግብ ጉድለት ለማቀቁ ልጆና ለነፍሰ-ጡር ሴቶች እርዳታ እየተደረገ ነው። የውሀ ጉድጓድም እየተቆፈረ ነው። ወሀ ለሚያስፈልጋቸው እንዲዳረስም እየተደርገ ነው። አርሶ አደሮች ዝናብ ሲገኝ የሚዘሩት እህልንም እያቀረብን ነው ሲሉ የቡድኑ ምክትል ሃላፊ አንደርሰን ገልጸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የለገሰችው መጠን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ከባድ ድርቅ ለማቃለል ከሚያስፈልገው ገንዘብ ጋር ሲወዳደር ያነሰ ስለሆነ ጥረታችሁ በገንዘብ እጥረት ምክንያት እንዳይሰናከል ስጋት አይኖርምን? ለሚለው ጥያቄ፣ “አስፈላጊ ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያ መንግስትና የሰብአዊ ረድኤት ድርጅቶች

ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል። 10 ሚዮን የሚሆኑ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚጠብቁ ናቸው። ተጨማሪ ስምንት ሚልዮን ደግሞ የምግብ ዋስትና የላችውም። 2.2 ሚልዮን የሚሆኑ ህጻናት በምግብ እጥረት የማሰኑ ናቸው። 450 ሺህ ህጻንት ደግሞ ከባድ የምግብ እጥረት ገጥሟቸዋል። የሚያስፈልገው ገንዘብ 1.5 ቢልዮን ዶላር ነው። ያለው ባጀት ግን ግማሹ ብቻ ነው። ስለሆነም የሚያስፈልገው ገንዛብ እስካሁን ከተሰጠው የበዛ ነው። ተጨማሪ የውጭ ረድኤት ያስፈልጋል ማለት ነው።”

ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት አመታት ተኩል ያህል በሰብአዊ ረድኤት ዘርፎች እንደሰሩ የተናገሩት አንደርሰን የዩናይትድ ስቴትሱ ቡድኑ መሪ ግን ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ እንደሰሩ የቡድኑ አባላት የሆኑ ኢትዮጵያውያንም እንዳሉበት አንደርሰን ሳይገልጹ አላለፉም። የድርቁን ችግር በማቃለል ተግባር ለመርዳት የሚፈልጉ ካሉ WWW.CIDI.org በሚል ድረ ገጽ ውስጥ ገብተው ኢንፎርሜሽን ለማግኘት እንደሚችሉ ጆናታን አንደርሰን ገልጸዋል።

በውጭ ሀገራት የተከሰቱ ቀውሶችን በማስወገድ ተግባር የሚረዳ የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ የልማት አገልግሎት ክፍል ከባድ አውሎ ነፋስን፣ ርዕደ-ምድርንና ድርቅን የመሳሰሉ ቀውሶች በደረሱባቸው የአለም ሀገሮች ሚረዳ ተቋም ነው።

የትግርኛ ክፍል ባልደረባችን በትረ ስልጥን ነው ያነጋገራቸው። አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ቀጥተኛ መገናኛ

ለኢትዮጵያ ድርቅ የአሜሪካ ተጨማሪ ድጋፍ፡ 268 + 500 ሚሊዮን ዶላርስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00

XS
SM
MD
LG