በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“እኔ መቼም የኦነግ አባል ሆኜ አላውቅም ” አቶ በቀለ ገርባ


የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ ከአራት ዓመታት በላይ ታሥረው ከቆዩ በኹዋላ በቅርቡ ተፈትተዋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ የነበሩት አቶ በቀለ ገርባ ከአራት ዓመታት በላይ ታሥረው ከቆዩ በኹዋላ በቅርቡ ተፈትተዋል። የተፈቱትም የተፈረደባቸውን የእሥራት ዘመን ጨርሰው ነው ተብሏል። በወቅቱ አብረዋቸው የታሠሩት የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግሬስ አመራር አባል አቶ ኦልባና ሌሊሣ ግን አሁንም በወህኒ ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ በቀለ ወደ ቀድሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ መምህርነት ሥራቸው የመመለስ እቅድ እንዳላቸውና ሁኔታዎች እስኪለወጡ ድረስ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ እንደሚቆዩም አረጋግጠዋል።

ስለ ግንቦቱ የኢትዮጵያ ምርጫና ስለ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ተጠይቀውም መልሰዋል።

“እኔ መቼም የኦነግ አባል ሆኜ አላውቅም ” አቶ በቀለ ገርባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG