በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ዝናብ ላይ ተመርኩዘን መኖር የለብንም" ረዳት ፕሮፌሰር ሳራ ተወልደ ብርሃን


የሚዘንብ ዝናብ ላይ ተመርኩዘን መኖር አለብን?
የሚዘንብ ዝናብ ላይ ተመርኩዘን መኖር አለብን?

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያን አርሶ አደርና አርብቶ አደር የዝናብ ውሃን ጠብቆ ነው የሚተዳደረው። በየአመቱ በሚዘንበው የዝናብ መጠን ማነስ ከአምራች ገበሬዎቹ ህይወት በተጨማሪ በምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ እጥረት ይገጥማል።

በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ የሚከሰተውን የውሃ እጥረት በተያያዥነትም ረሃብና ድርቅ እንዴት ለመቋቋም እንደሚቻል የተለያዩ የውሃ አጠቃቀም ዘዴዎች ሲተገበሩ ቆይተዋል። የውሃ እጥረት ችግርን በኢትዮጵያ ለመቅረፍ ከዝናብ የምናገኘውን ውሃ በበቂ ሁኔታ እየተንከባከብን የሚዘንበውንም ዝናብ አቁረን በመያዝ ወንዞችና ምንጮች እንዲጎለብቱ በማድረግ ችግሩን ለመቀነስ እንዲሁ ለማስቀረት እንችላለን ስትል በመቀሌ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር፣ እንዲሁም የደንና የምግብ ሳይንስ ባለሙያ ሳራ ተወልደ ብርሃን አስተያየቷን ሰጥታናለች። በአለም አቀፉ የአየርንብረት መዛባትና በኢትዮጵያ እየተከሰት ስላለው የውሃ እጥረት ዙሪያም ችግሩን ለመቅረፍ ምን መደረግ እንዳለበት በአጭሩ አስረድታለች።

በአለም እየተከሰተ ስላለው አየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዋፆ ለማድረግ ዛፎችን በመትከልና የነበሩትን በመንከባከብ ለአየር ንብረት ደህንነት መንቀሳቀስ መጀመር ይቻላል።

እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ግለሰብ አሁን እየተከሰተ ያለውን የውሃ እጥረት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ ምን ቢያደርግ የተሻለ ነው ለሚለው ጥያቄ ሙያዊ አስተያየቷን ሳራ ተወልደብርሃን አካፍላናለች።

ከመስታወት አራጋው ጋር ያደረገችውን አጭር ቆይታ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።

ህጻናት አትክልት እየተከሉ /ፋይል ፎቶ - ከትሪስ ፎር ዘ ፉውቸር የተባለ ድርጅት የፍሊከር አካውንት የተገኘ ፎቶ/
ህጻናት አትክልት እየተከሉ /ፋይል ፎቶ - ከትሪስ ፎር ዘ ፉውቸር የተባለ ድርጅት የፍሊከር አካውንት የተገኘ ፎቶ/

"የሚዘንብ ዝናብ ላይ ተመርኩዘን መኖር የለብንም" ረዳት ፕሮፌሰር ሳራ ተወልደ ብርሃን
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG