በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥት የሀይል እርምጃ ከቀጠለ የሀገሪቱ ሁኔታ የከፋ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች አስጠነቀቁ


የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሊቀመንበር እና የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሊቀመንበር እና የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን

የመንግሥት የሀይል እርምጃ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ሀገሪቱ ወደ ከፋ ሁኔታ ልታመራ ትችላለች ሲሉ ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል።

መንግሥት ኃላፊነቱን ሊገነዘብና የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ያሉት የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚተ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ ናቸው።

ተመሣሣይ ሃሳብ ያስንጸባረቁት የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ በባህርዳር የተገደሉት ሰዎች ቁጥር በብዛት ጨምሯል ብለዋል።

መንግሥት በበኩሉ ለዚህ ተጠያቂዎቹ የህውከት ሀይሎች ያላቸው መሆናቸውን ሲገልጽ ቆይቷል።

የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሊቀመንበር እና የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በባህር ዳር የሰጡትና በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን የተዘገበው መግለጫ ከሰሞኑ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በኃላ የመጀመርያው ነው።

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበር ድርጅታቸው ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያይዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የመንግሥት የሀይል እርምጃ ከቀጠለ የሀገሪቱ ሁኔታ የከፋ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች አስጠነቀቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG