በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮሙስሊምግሎባልዶትኢቲ


የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ታሪክ በመዘከርና በማስተዋወቅ ለሃገር ሰውና ለመላው ዓለም መረጃ ይሰጣል የተባለ ዌብሣይት በሸራተን ሆቴል በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

www.ethiomuslimglobal.et በሚል አድራሻ የተከፈተው ዌብሣይት በርካታ ዓላማዎች እንዳሉት ተገልጿል፡፡

የዌብሣይቱ ሥራአስኪያጅና የኦፐሬሽን ኃላፊ ያሲን ራጂ በተለይ ማንን መድረስ እንደሚያስቡ ሲናገሩ "ሙስሊሙ ኅብረተሰብ እንደማንኛቸውም ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን መብቱንና ግዴታውን አውቆ ለሃገሩ ልማት፣ መቻቻል፣ ታሪክ፣ ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንት፣ ቅርስ፣ ከመረጃ ምንጮች የተገኙ የሃገራችንን ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች በሃገር ውስጥ እና በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፣ በመላው ዓለም ለሚገኘው ሕዝብ በተለይ ለሁለት ቢልዮን የዓለም ሙስሊም፣ ለሦስት መቶ ሚሊዮን አረብኛ ተናግጋሪዎች .... እውነተኛ መረጃ ለመስጠት ዌብሣይታችን ዝግጅቱን አጠናቅቋል" ብለዋል፡፡

ዌብሣይቱ በአማርኛ፣ በዐረብኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ባለውለታዎችን ማቅረብ፣ መዘከር ከዓላማዎቹ መካከል እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG