በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ቁጣ

ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይደርስብናል የሚሉትን የዘረኝነት መድልዎህ የፖሊስ ጭካኔ የሚያጣራ የመንግሥት ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተቋቁሟል፡፡

ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ጊዜ ከፖሊስ ጋር የተፈጠረ ግጭት
ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ጊዜ ከፖሊስ ጋር የተፈጠረ ግጭት

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይደርስብናል የሚሉትን የዘረኝነት መድልዎህ የፖሊስ ጭካኔ የሚያጣራ የመንግሥት ኮሚቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተቋቁሟል፡፡

የቤተ-እሥራኤላዊያኑ ችግር መድኃኒት ሊፈለግለት የሚገባ “ክፍት ቁስል” ነው ሲሉ የእሥራኤል ፕሬዚዳንት ሩቨን ሪቭሊን ዛሬ አስታውቀዋል፡፡

ትናንት በሺሆች የሚቆጠሩ እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል፡፡

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ማኅበረሰብ አባላት ጋር ዛሬ ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል
እሥራኤላዊያኑ የኢትዮጵያ አይሁድ በማዕከላዊ ቴል አቪብ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተው ዋናውን አውራ ጎዳና ለረዥም ሰዓት ዘግተዋል

ፕሬዚዳንት ሪቭሊን በዛሬው መግለጫቸው “አላስተዋልንም፤ በቅጡ አላዳመጥንም፡፡ እኛ’ኮ እርስ በራሣችን ባይተዋር አይደለንም፤ ወንድማማች ነን፡፡ በኋላ ሁላችንም ወደሚያሳዝነን ወይም ሊቆጨን ወደሚችል ደረጃ ልንዘቅጥ አይገባንም” ብለዋል፡፡

ችግሮቹና በደሎቹ እንዳይደገሙ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎችም ዛሬ የተቋቋመው ኮሚቴ ይተልማል ተብሏል፡፡

የተቃውሞ ሰልፎቹ የተጀመሩት ባለፈው ሣምንት የእሥራኤል ፖሊሶች አንድ የደንብ ልብስ የለበሰ የኢትዮጵያ ዝርያ ያለውን የራሣቸውን ወታደር ክፉኛ ሲደበድቡ የሚያሣይ ቪዲዮ ከወጣና ከተሠራጨ በኋላ ነው፡፡

እሥራኤል ውስጥ ከ135 ሺህ በላይ ትውልደ-ኢትዮጵያ ቤተ-እሥራኤል ይኖራሉ፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG