በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ለአሜሪካ ሴኔት እየተወዳደሩ ነው


ትውልደ-ኢትዮጵያው ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ለዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነት ቴክሳስ ግዛት ላይ እየተወዳደሩ ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ለአሜሪካ ሴኔት እየተወዳደሩ ነው
ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ለአሜሪካ ሴኔት እየተወዳደሩ ነው

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ትውልደ-ኢትዮጵያው ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ለዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባልነት ቴክሳስ ግዛት ላይ እየተወዳደሩ ናቸው፡፡

በተወካዮች ምክር ቤት 435 የሕግ መምሪያው መቀመጫዎች እና በሕግ መወሰኛው ውስጥ ደግሞ ከመቶዎቹ መቀመጫዎች ሲሦ ያህሉ ናቸው ዛሬ ምርጫ እየተካሄደባቸው ናቸው፡፡

ፕሮፌሰር መሐመድ የሚወዳደሩት በግላቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ፕሮፌሰር መሐመድ ለሴኔቱ እንደሚወዳደሩ ያሳወቁ ጊዜ ብዙ ሰው እንደ ዕብደት እንቆጠረባቸው አስታውሰው “በማንኛውም ጊዜ ወደ አሜሪካ የገቡና የአሜሪካን ዜግነት የወሰዱ ሰዎች ሃገራቸው ናትና የመምረጥና የመመረጥ መብታቸውን መጠቀምና ማስከበር አለባቸው” ብለዋል ዕጩ እንደራሴው፡፡

ፕሮፌሰር መሐመድ ሐይማኖታቸውን አስመልክቶም ሙስሊም በመሆናቸው ምክንያት ከውድደሩ እንዲወጡ ስልክ ደውለው መልዕክት የተዉላቸውን አንድ የሪፐብሊካን ፓርቲው አባል የሆኑ ሰው ጨምሮ አንዳንድ እርሣቸው “ጥሩ ያልሆኑ” ያሏቸው ሰዎች ቢኖሩም እነዚያ ግን በአጠቃላይ “በጣም ጥሩ ነው” ያሉትን የቴክሳስን ሕዝብ የሚወክሉ አለመሆናቸውንና ተስፋም እንደማያስቆርጧቸው ተናግረዋል፡፡

ለዝርዝሩ ፕሮፌሰር መሐመድ ጣሂሮ ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG