በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴሌኮም 28 ቢሊዮን አስገባ


በ2008 የበጀት ዓመት የ28 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስገባቱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ።

አብዛኛው ገቢ ከተንቀሳቃሽ ወይም ከሞባይል ስልክ የተገኘ መሆኑንም ታውቋል።

ዓለምአቀፍ ተቋማት በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይሰጡ መንግሥት የሚከለክለው ይህንን መሰል ገቢ ስለሚያገኝ ነው የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ከዓመት ዓመት እያደገና ገቢው እየጨመረ መሄዱን ገልጿል።

በዓመቱ ያገኘው ገቢ 28 ቢሊዮን ብር መሆኑን ጠቅሶ ይህ ገቢ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 30 ከመቶ ማደጉን የድርጅቱ መግለጫ ጠቁሟል።

ዝርዝር ዝገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ቴሌኮም ሁለት ቢሊዮን አስገባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:42 0:00

XS
SM
MD
LG