በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያንና ኬንያን የሚያገናኝ አውራ ጎዳና እንዲገነባ ውል ተፈረመ


ኢትዮጵያንና ኬንያን የሚያገናኝ አውራ ጎዳና እንደሚገነባ ተገለጸ። ከሞምባሳ እስከ ናይሮቢ ከናይሮቢ እስከ አዲስ አበባ ባለው መስመር ላይ ለሚካሄደው ለዚሁ የመንገድ ግንባታ የሚሆን የ $743 ሚልዮን ዶላር ብድር ከአፍሪቃ የልማት ባንክ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙኒኬሽንስ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ወንድሙ "ከአዲስ አበባ ሀዋሳ ያለው መንገድ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል። እናም በኢትዮጵያ በኩል የሚጠበቀው ከሀዋሳ እስከ ሞያሌ ያለውን ክፍል በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃውን ማጠናከር ነው ሲሉ አስረድተዋል። ከሞያሌ እስከ ሞምባሳና ናይሮቢ ያለው የመንገድ ክፍል ደግሞ የኬንያውያን ድርሻ መሆኑን አቶ ሳምሶን ውንድሙ አክለዋል።

XS
SM
MD
LG