በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የሰብአዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን ዘገባ በመቃወም ኤርትራዊያን በጀኔቫ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱ


የተመድ የሰብአዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን ዘገባ በመቃወም ኤርትራዊያን ሰላማዊ ሰልፍ - በጀኔቫ
የተመድ የሰብአዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን ዘገባ በመቃወም ኤርትራዊያን ሰላማዊ ሰልፍ - በጀኔቫ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስለ ኤርትራ ጉዳይ ጥናት እንዲያቀርብ የተመሰረተው ኮሚሽን የኤርትራ መንግስት ለ25 አመታት ያህል ሰፊ ይዘት ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣ ሲያከናውን ቆይቷል። ይህም በስብእና ላይ የተፈጽሙ ወንጀሎች ደረጃ ተደርጎ ይታያል ሲል ከ 14 ቀናት በፊት ባወጣው ዘገባ መግለጹ የሚታወስ ነው።

ዛሬ ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ካውንስል አባላት የሰብአዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን ባቀረበው ዘገባ ላይ ሃሳባቸውን እየሰጡ ነው። ይህን ውሳኔ የሚቃወሙ ኤርትራውያን በጄኔቫ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሄዱ ውለዋል። እስራኤል ውስጥ ደግሞ መርማሪው ኮሚሽን ያወጣውን የሚደግፉ ኤርትራውያን ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተሰይመው ስለኤርትራ ጉዳይ ጥናት ያቀረቡት ኮሚሽነሮች ኤርትራ በፍጹማዊ አገዛዝ የምትገዛ ሃገር ናት። ከመንግስታዊ ተጽእኖ ነጻ የሆነ የፍርድ ስርአት፣ ብሄራዊ ሸንጎ ወይም ዲሞክራስያዊ ተቋማት የሏትም ይላሉ። በህዝቡ ላይ የፍርሀት ድባብ በማስፈን የፖለቲካ ተቃውሞን ለማስወገድ ሲባል የባርነት ወንጀልን፤ እስራትን፤ እንደወጡ መቅረትን የመሳሰሉት ሁኔታዎች ይፈጸማሉ ሲሉም ኮሚሽነሮቹ ጠቁመዋል።

መርማሪዎቹ አያይዘውም ጎብኚዎች በኤርትራ ላይ ላዩን በሚያዩት የአስመሳይ ሰላም መታለል የለባቸውም ብለዋል። የመርማሪው ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማይክ ስሚት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ሲናገሩ አስመራን የሚጎበኙ ሰዎችም ሆኑ እዛ የሚኖሩ የውጭ ሃገራት ተወላጆች ለየት ያለ ገጽታ ነው የሚታያቸው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የተመድ የሰብአዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን ዘገባ በመቃወም ኤርትራዊያን በጀኔቫ ሰላማዊ ሰልፍ ኣካሄዱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG