በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራው ፕሬዚደንት መንግሥታቸው በልዩ ልዩ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ዙሪያ በሚከተላቸው ፖሊሲዎች ላይ ማብራሪያና ገለጻ አደረጉ


የኤርትራው ፕሬዚደንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥታቸው በልዩ ልዩ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ዙሪያ በሚከተላቸው ፖሊሲዎች ላይ ማብራሪያና ገለጻ አደረጉ።

በኤርትራው ቴሌቪዥንና ዲምጺ ሃፋሽ ራድዮ በተላለፈው የፕሬዚደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ገለጻና ማብራራያ ባለፈው እአአ 2015 ዓ.ም. የተገኙ የልማት ዕድገቶችና ውጤቶችን እንዲሁም በአሁኑ እአአ 2016 ዓ.ም. የተያዙ ዕቅዶችንም የሚያጠቃልል ንግግር ተናግረዋል።

ኤርትራ አዲስ ባወጣች የናቅፋ ኖት ላይ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ባደረጉት ገለጻ፣ አዲሱ ኖት ከመውጣቱ አስቀድሞ አስፈላጊው መሰናዶና ዝግጅት መደረጉን አስመልክተው ፕሬዚደንት ኢሳያስ፣ "አላማው ኢኮኖሚውን ለመስተካከል ተብሎ ሲሆን ይህንን አሰራር ለማገዝ ከሚችሉ መሳርያዎች አንዱ ገንዘብ ነው። ሁሉም የኢኮኖሚ ጉዳይ ገንዘብ በመቀየር ይስተካከላል ማለት ሳይሆን፣ እሱ እንደ መጀመርያ ሆኖ ሌሎች ብዙዎች የተዛቡ ጉዳዮች ለማስተካከል ይቻላል"ብለዋል።

የአዲስ ናቅፋ መውጣት፣ ለአገሪቱ ኤክኖሚ አዲስ ተዓምር ይፈጥራል ማለት አለመሆኑን አበክረው የተናገሩት ፕሬዚደንት ኢሳያስ፣ ዳሩ ግን "መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማሳደግ ተጨማሪ ጥረት ያደርጋል ዋስትናም ይሰጣል" ብለዋል።

ፕሬዚደንት ኢሳያስ ስለ ኢትዮጵያው ህዳሴ ግድብም፣ "እኔ ባጠቃላይ ግልጽ ያልሁነ፣ ከመጀመርያውኑ ለፖለቲካዊ መሳርያ ተብሎ የተጀመረ ስለሆነ፣ ቢመሰረትም ባይመሰረትም በሚያስከትለው እንደምታ ዋና ተጎጅው ወገን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። ይህ ጉዳይ ተጨርሷል ሰአቱ ደርሷል መጨረሱ አይቀአርም ከአመት ከሁለት አመት በኋላ ስራ ይጀምራል" የሚባለውን ዘገባ "እንደ እውነታ መቀበል ያለብን ጉዳይ ነው" ብለዋል።

በመቀጠልም "እንደ እውነታ ከመቀበል በኋላስ? እኔ በበኩሌ ካለ ስብሰባና ስሜት በተሞላበት ነገ ዛሬ ያልቃል ከማለት በስተቀር፣ ቁም ነገሩን እንደምገልጸው መረዳት ያለብን ጉዳይ ነው" ብለው እንደምያምኑ ገልጸዋል። "እኛ፣ በተለይም እኔ በቅርብ የተከታተልኩት ጉዳይ ነው። የኤርትራ ህዝብም በደምብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ይህ ፕሮጀክት ሲጀመር እንዴት እንደ ተጀመረ ስለምናውቅ አሁን የሚያነጋግረው ያለው ጉዳይ ለህዝብ ግንኙነት ፍጆታ ጊዜ ለማጥፋት የሚደረግ ነው። የሚከተለውን ችግርና ጉዳት ግን ሰፋአድርጎ የሚያናግርበት ደረጃ አልደረሰም" ብለዋል።

ባለፈው ዓመት የነበረው ድርቅና የአዝመራ አለመሳካት፣ መላውን የአፍሪቃ ቀንድ እንደጎዳ ይታወቃል። ከዚያ አኳያ ኤርትራ ውስጥ ስለነበረው የምግብ ሁኔታ ፕሬዚደንት ኢሳያስ ሲናገሩ፣ "ችግር የለም ስል ማጋነን እንዳይመስል እንጂ ባለፉት አመታት ቀጣይ በርከት ያለ ዝናብ ስለነበረ ብቻ ሳይሆን፣ አሰራራችንም ይጠቅመናል ብለን ተዘጋጅተን ስንሰራ ስለ ከረምን ነው። ሌሎች አገሮች የአምስትና የአስር አመት መጠባበቅያ የሚሆን ምግብ ይዘው በመቆየት ሰዎች ሲርባቸው ብቻ ማደል ቢጀምሩም እኛ እንደሱ አይነት ሁናቴ ላይ ነገሮች ሳይደርሱ ችግር እንደሚመጣ ግምት ውስጥ በማስገባት ችግሮችን ለመወጣት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን አድርገን ችግሮችን ለመወጣት ዝግጁዎች መሆን ስላለብን ነው። ይህ አሰራር ጥሩ ልምድ ያካበትንበት አሰራር ስለሆነ እስካሁን የሚያሳስብ ሁናቴ አልታየም" ብለዋል።

ኤርትራና ኢትዮጵያ
ኤርትራና ኢትዮጵያ

በመጨረሻም ስለ ውጪ ፖሊሲያቸው ሲናገሩ፣ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ስለጀመሩት የፀረ-ሽብር ትብብር ማለትም የመን ውስጥ ያሉትን ሽምቅ ተዋጊዎች ለመውጋት ስላላቸው ዕቅድ ይህን ብለዋል።

"በዚህ አካባቢ የሚገኙ አገሮችም ሆኑ መንግሥታት ዋና ሃላፊነት መሸከም የሚገባቸው አካሎች የአካባቢውን እርጋታ ለመጠበቅ ረብሻ ሊያስከትሉ በሚችሉ መንስኤዎች ላይ እርምጃ መወሰድ አለባቸው። እንደዛም ስለሆነ አዋጅ ከተደረጉት የፀረ-ሽብር ውሎች ውስጥ እስካሁን ምንም ለውጥ ያላየንባቸው አዋጆች ናቸው። ነገር ግን የአከባቢው አገሮች የሚያደርጉት ጥረት ስለሚያዋጣ ከሳዑዲ ጋርም ሆነ ሌሎች በዚህ አካባቢ የሚገኙ ሽሪኮቻችን መምታት የምንፈልገውን አላማ በአንድ ላይ ሆነን የምንሰራበት ጉዳይ ነው። ይህ በሳዑዲ የወጣው የፀረ-ሽብር ትብብር ከታላቅ ሌሎች መደቦች ውስጥ አንድ ትንሽ መደብ ነው ማለት እንችላለን" በማለት በቴሌቪዥን ቃለ-ምልልሳቸው አስረድተዋል።

ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG