በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የገዥው ፓርቲና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ድርድር የአጀንዳ አደራጅ ሥራውን ጀመረ


ኢሕአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር
ኢሕአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅድመ ድርድር

ከገዥው ፓርቲና ከሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ለድርድር የቀረቡ አጀንዳዎችን የሚያጠናቅረው የአጀንዳ የአደራጅና የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ ዛሬ ሥራውን ጀምሯል፡፡

ከገዥው ፓርቲና ከሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ለድርድር የቀረቡ አጀንዳዎችን የሚያጠናቅረው የአጀንዳ የአደራጅና የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ኮሚቴ ዛሬ ሥራውን ጀምሯል፡፡ ድርድሩ ሊጀመር የሚችለው ፓርቲዎቹ በተደራጁት አጀንዳዎች ላይ ከሥምምነት ከደረሱ በኋላ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በተቃዋሚ ፓርቲዎች ከቀረቡት አጀንዳዎች መካከል የፖለቲካና የሕሊና እሥረኞች መፈታትና የፀረ ሽብር ሕጉ መሻሻል እንደሚገኝበት የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል፡፡

በገዥው ኢህአዴግና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል የሚደረገው ድርድር በሚመራበት ሠነድ ላይ ከሥምምነት በመደረሱ አሁን ትኩረቱ በአጀንዳዋች ላይ ሆኗል፡፡ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎቹ በምን በምን ጉዳዮች ላይ እንደሚደራደሩ ገና አልተወሠነም፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የገዥው ፓርቲና ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ድርድር የአጀንዳ አደራጅ ሥራውን ጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG