በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤል-ኒኞ እንደበረታ ይቆያል


በአሁኑ ጊዜ ተንሠራፍቶ ያለውና በዓለም ዙሪያ ብዙ ጉዳት እያስከተለ ያለው የኤል-ኒኞ ክስተት ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያና በሌሎችም የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች ውስጥ ጊዜውን ያልጠበቀ የአየር ርጥበትና ዝናብ የሚስተዋለው የውቅያኖሱ ውኃ እንደሞቀ የሚገኝ በመሆኑ ነው ሲሉ ከቪኦኤ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረጉት የኢትዮጵያ ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ ሻንቆ አስታውቀዋል፡፡

ሰብል የደረሰላቸውና የሚሰበስቡ ሁሉ ማሣ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ከዝናብ አደጋ ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አቶ ዱላ አሳስበው የሚሰበሰበውንም ሆነ ተወቅቶ ጎተራ መግባት ያለበትን ለማጠናቀቅ ሰዉ ደቦን በመሣሰሉ ማኅበራዊና ባሕላዊ ልማዶቹ አማካይነት እንዲረባረብ መክረዋል፡፡

የኤል-ኒኞው ሁኔታ ቢያንስ ለመጭዎቹ ሦስት ወራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከፊታችን ኅዳር 20 እስከ ታኅሣስ 1 / 2008 ዓ.ም ፓሪስ ላይ የሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ዓለማችንን ለመጠበቅ የሚያስችል አንዳች ስምምነት ላይ ይደረሣል ብለው እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተቋቋመው የዓለምአቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ዓለምአቀፍ ቡድን - አይፒሲሲ የኢትዮጵያ ማዕከል መሆኑንና ኢትዮጵያም ለፓሪሱ ጉባዔ በሚደረገው ዝግጅት ከሦስቱ የአይፒሲሲ የሥራ ቡድኖች አንዱን በምክትል ሊቀመንበርነት እየመራች መሆኗን አቶ ዱላ ገልፀዋል፡፡

ለሙሉው ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኤል-ኒኞ እንደበረታ ይቆያል
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:04 0:00

XS
SM
MD
LG