በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት የማይታጠፍ ጫና ኢትዮጵያ ላይ እንዲያሳድር ተጠየቀ


አና ጎሜዥ
አና ጎሜዥ

በኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት የታሠሩት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና የተገኙበትን የአውሮፓ ፓርላማ የእማኝነት መስሚያ መርኃ ግብር ያዘጋጁትና ግብዣውንም ያደረጉት የፓርላማው አባል አና ጎምሽ የአውሮፓ ፓርላማ የዶ/ር መረራን እሥራት በብርቱ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል፡፡

ዶ/ር መረራ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያለማወላወል ጫና እንዳያሳድሩና መታሠራቸው በራሱ ኢትዮጵያ ግዴታ የገባችባቸውን የኮቶኑ ስምምነት የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች የጣሰ መሆኑን የኅብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሞጌሪኒ አጢነው በብርቱ እንዲያወግዙት አና ጎምሽ አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና /ፎቶ ፋይል/
ዶ/ር መረራ ጉዲና /ፎቶ ፋይል/

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የሪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን የብር ሜዳልያ አሸናፊው ፈይሣ ሌሊሣ የአውሮፓ ፓርለማ መቀመጫ ወደሆነችው የቤልጅግ ዋና ከተማ ብራስልስ ሄደው በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ እማኝነታቸውን እንዲሰጡ የጋበዙ፣ መድረኩንም ያዘጋጁት አና ጎምሽ የዶ/ር መረራ መታሠር “ቢያስደነግጠኝም አልገረመኝም” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ ዘገባውንና ከአና ጎምሽ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል የያዘውን ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት የማይታጠፍ ጫና ኢትዮጵያ ላይ እንዲሳያድር ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:37 0:00
ከሚስ አና ጎምሽ ጋር የተደረገ ሙሉ ቃለ ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:24 0:00

XS
SM
MD
LG