በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሀሙሱ የዋሽንግተን ዲሲ የድጋፍና የተቃውሞ ሰልፍ የመነጋገሪያ ነጥቦች


የመንግስት ደጋፊዎች ከአንድ ተቃዋሚ ጋር ተጋጭተዋል።
የመንግስት ደጋፊዎች ከአንድ ተቃዋሚ ጋር ተጋጭተዋል።

ከዋይት ኃውስ ቤተመንግሥትና ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጃፍ የወጡት በአንደኛው ጎራ የኢትዮጵያን መንግስት በመደገፍ ሲሰለፉ፤ እዚሁ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኙት የቻይናና የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ፊት ለፊት የተሰለፉት ደግሞ ሁለቱን መንግስታት በመቃወም የወጡ ናቸው።

ዶ/ር ከፋለ ገብረ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያን መንግስት ለመደገፍ ከተደራጀው ቡድን ሲሆኑ አቶ ኢሳያስ ልሳኑ ደግሞ በተቃውሞ ከተሠለፈው ወገን ናቸው።

በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ያላቸውን አቋም ለመግለፅ፥ በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የፀረ ሽብር ትብብር እንዲቀጥል ያላቸውን አስተያየት ለማንፀባረቅና እንዲሁም የግንቦቱ ምርጫ በተሳካ መልኩ በመጠናቀቁ ለስኬቱ አስተዋፅኦ ያደረገውን የኢትዮጵያን ህዝብ ለማመስገን መውጣታቸውን ዶክተር ከፍ ያለ ሲገልፁ፤ አቶ ኢሳያስ በበኩላቸው፥ የቻይና መንግስት በህዝቡ ላይ “የጭቆና ቀንበር እየጫነ ላለው” ላሉት የኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠውን ድጋፍ በመቃወም መሠለፋቸውን ይናገራሉ።

በእሰጥ አገባ ዝግጅት ተከራክረዋል።

XS
SM
MD
LG