በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሲፒጄ የኢትዮጵያን መንግሥት በሚድያ አፋኝነት ከሠሠ


የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያላቸው አያያዝ አፋኝ እና እጅግ የከፋ ነው ሲል ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት - ሲፒጄ አስታወቀ፡፡

የሲፒጄ እና የአፍሪካ ሚድያ ኢኒሼቲቭ የቦርድ አባላት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምዖን ጋር ተገናኝተው ነበር፡፡

የቦርድ አባላቱ በዚህ ስብሰባቸው ወቅት በሃገሪቱ ውስጥ የታሠሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሠር ከጎረቤቷ ከኤርትራ ቀጥላ በአፍሪካ ሁለተኛ ሃገር መሆኗን ድርጅቱ አመልክቷል፡፡

ይህ አዲስ አበባ ላይ የተካሄደው የሁለት ሰዓት ስብሰባ ያተኮረው ኢትዮጵያ ባሠረቻቸው በእነዚህ ጋዜጠኞችና የኢትዮጵያ መንግሥት ለነፃው መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ባለው አጠቃላይ አያያዝ ላይ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሲፒጄ ባለሥልጣናት በፅሕፈት ቤቱን ኃላፊ ለማነጋገር በጠየቁት መሠረት ሚኒስትሩን ማግኘታቸውን የመሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺመልስ ከማል ጠቁመው የሲፒጄ ተወካዮች ከርቀት የውግዘት መግለጫዎችን ከማውጣት ይልቅ ሁኔታውን በቅርብ በተግባር የሚያዩ ልምድ ያላቸውን ሰዎች ጠርቶ የቅርብ መግባባትን ለመፍጠር ያደረገውን ጥረት ሚኒስትሩ ማመስገናቸውን ገልፀዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አቶ ሺመልስ አክለውም “ኢትዮጵያ ውስጥ በፃፈው ወይም በተናገረው ምክንያት የታሠረ ጋዜጠኛ የለም” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG