በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ርዕሰ አንቀጽ፡ "ጋዜጠኞች ዛሬም የጥቃት ዒላማ ናቸው"


ፋይል ፎቶ - አንድ ስደተኛ በእስራኤል ወስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ [እአአ 2014 አሶሽየትድ ፕረስ/AP]
ፋይል ፎቶ - አንድ ስደተኛ በእስራኤል ወስጥ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ [እአአ 2014 አሶሽየትድ ፕረስ/AP]

ለጋዜጠኞች መብት የቆመው ዓለም አቀፍ ድርጅት (CPJ) እንዳመለከተው፤ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም. ብቻ በዓለም ዙሪያ ከስልሳ በላይ ጋዜጠኞች ተገድለዋል። ንግግርን የመግለፅ ነፃነት አደጋ ላይ ይገኛል፣ "ጋዜጠኞች ዛሬም የጥቃት ዒላማ ናቸው" ሲል፤ ይንደረደራል፤ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

“በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ፥ በቬዬትናም፥ በሶሪያ፥ በኢራንና ሌሎች አገሮች ጋዜጠኞች ዛሬም የጥቃት ዒላማ ናቸው። የንግግር ነጻነት አደጋ ላይ እንደ ወደቀ ነው።” ሲል፤ ይንደረደራል፤ የዕለቱ ርዕሰ አንቀጽ።

ለጋዜጠኞች መብት የቆመው ዓለም አቀፍ ድርጅት (CPJ) እንዳመለከተው፤ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2014 ዓ.ም. ብቻ በዓለም ዙሪያ ከስልሳ በላይ ጋዜጠኞች ተገድለዋል። በብዙ መቶዎች ታስረዋል፤ በርካቶችም የገቡበት አልታወቀም።

ሌላው ለጋዜኞች መብት የቆመው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን (Reporters without Borders) መንግስታት የጋዜጠኞችን ድምጽ ለማፈን የሚጠቀሙባቸው መንገዶች፤ ሳንሱርን፥ ወከባን፥ መንግስታዊ ባልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ላይ የሚጣሉ ገደቦችንና የፖለቲካ መሪዎች መግልጽ የሚሰነዝሯቸውን ዛቻዎች ይጨምራሉ፤ ይላል።

ርዕሰ አንቀጹን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ርዕሰ አንቀጽ፡ ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት አደጋ ላይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:49 0:00

XS
SM
MD
LG