በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“በመቃወም ብቻ ቢኾን ኖሮ ዶ/ር መረራ ይታሠሩ ነበር” የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ

Getachew Reda, Ethiopia Government Spokesman
Getachew Reda, Ethiopia Government Spokesman

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትም ኾነ የሰማያዊው ፓርቲ ወጣቶች የታሠሩት፤በወንጀል ተጠርጥረው እንጂ በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ስለተሳተፉም ኾነ ስለጻፉ አይደለም ሲሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮቸ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትም ኾነ የሰማያዊው ፓርቲ ወጣቶች የታሠሩት፤በወንጀል ተጠርጥረው እንጂ በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ስለተሳተፉም ኾነ ስለጻፉ አይደለም ሲሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮቸ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ፤ በዛሬው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፤ ሰዎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ስገለጹ ብቻ አይታሠሩም፣የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላትም ኾነ የሰማያዊው ፓርቲ አባላት የታሠሩት ከጀርባ ካሉ ኃይሎች ትእዛዝ እየተቀበሉ ወንጀል ሲሠሩ በመገኘታቸው ነው ብለዋል፡፡ ሰዎች በመቃወማችው ብቻ ቢታሠሩ ኖሮ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይታሠሩ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በጥይት የተመቱ ሰዎች አስክሬን ገንዘብ እየተከፈለ ስለሚወሰድበት መንገድ የተነገረውን በሚመለከት ተጠይቀው ፤በቀይ ሽብር ጊዜ ተደርጓል የሚባልን ነገር ልክ እንደ ማስታወቂያ በመደጋገም እውነት ለማስመሰል የሚደረግ ነው በማለት አስተባብለዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳን ያነጋገረቻቸው ጽዮን ግርማ ነች፡፡

ቃለምልልሱን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“በመቃወም ብቻ ቢኾን ኖሮ ዶ/ር መረራ ይታሠሩ ነበር” የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG