በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጋምቤላ 12 ሕፃናት ታፍነው ወደ ደቡብ ሱዳን ተወስደዋል


የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት በ2008 ወስደው ከጋምቤላ ክልል ወስደው ካልመለሷቸው 57 ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ 12 ሕፃናት መውሰዳቸውን፣ እንዲሁም ከ16 በላይ ሰው መግደላቸውንና ከብቶች መዝረፋቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።ጥቃቱ እስከ ትናንት ምሽት መቀጠሉና በትናንትናው ዕለት አንድ ሕፃን ተወስዶ አንድ አዛውንት መገደሉ ጨምሮ አስታውቋል። የጋምቤላ ክልል ተወላጆች ይህ ችግር በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ያለው መንግስት ለዜጎቹ ጥበቃ ስለማያደርግ ነው ይላሉ።

የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት በተከታታይ ባካሄዷቸው የድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶች በሰው ህይወት ጉዳት ካደረሱ በኋላ ተጨማሪ ህጻነትን አፍነው መውሰዳቸውን የጋምቤላ ክልል መስተዳድር አስታወቀ።

የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዬች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኦኬሎ ኡማን ዴንግ ከመስከረም ወር ጀምሮ በደረሱ ጥቃቶች 16 ሰዎች ሲገደሉ ከ12 ህጻናት በላይታግተው መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ጥቃቱ እስከ ትናንት ማታ መቀጠሉን የገለጹት ኃላፊ ከዚህ ቀደም ተወስደው ከነበሩት 200 ሕፃናት 57ቱ እስካሁን አልተመለሱም ብለዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የጋምቤላ ክልል ተወላጆችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ይህ ችግር በተደጋጋሚ እየተፈጠረ ያለው መንግስት ለዜጎቹ ጥበቃ ስለማያደርግ ነው ይላሉ።

ጽዮን ግርማ ዝርዝሩን ይዛለች።

ከጋምቤላ 12 ሕፃናት ታፍነው ወደ ደቡብ ሱዳን ተወስደዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

XS
SM
MD
LG