በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮምያ ጉዳይ የሲቪከስና የአምነስቲ መግለጫና አቋም


የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ [ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ]
የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ [ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ]

የኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች ኦሮምያ ውስጥ ተገድለዋል ያሏቸውን 140 ሰዎች ጉዳይ በቅርበት እንዲፈትሹ ሲቪከስ ተብሎ የሚጠራው የዜጎች ተሣትፎ ዓለምአቀፍ ጥምረት ጥሪ አሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች ኦሮምያ ውስጥ ተገድለዋል ያሏቸውን 140 ሰዎች ጉዳይ በቅርበት እንዲፈትሹ ሲቪከስ ተብሎ የሚጠራው የዜጎች ተሣትፎ ዓለምአቀፍ ጥምረት ጥሪ አሰምቷል፡፡

ሲቪከስ የዛሬ 23 ዓመት የተመሠረተ ዓለምአቀፍ ጥምረት ነው፡፡

ሲቪከስ በመላው ዓለም የዜጎችን የተግባር እንቅስቃሴና ሲቪሉን ማኅበረሰብ ለማጠናከር በሚል ዓላማ የተመሠረተ፤ ዛሬ በ145 ሃገሮች ውስጥ አባላት ያሉት፤ ዋና ፅሕፈት ቤቱ ጆሃንስበርግ - ደቡብ አፍሪካ የሆነና ለንደን፣ ጄኔቫና ኒው ዮርክ ቢሮዎችን ከፍቶ እየሠራ ያለ ተቋም ነው፡፡

የሲቪከስ የምሥራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ የመብቶች ዘብ ወይም “ለዘቦች ዘብ ቁሙ” በሚል የተሰየመው ፕሮጀክት እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሚባለው ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን ሐሙስ፤ ጥር 15/2016 ዓ.ም ባወጡት መግለጫ ለኢትዮጵያ የልማትና ዓለምአቀፍ አጋሮች አቤቱታ አሰምተዋል፡፡

ሲቪከስና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በየዌብ ሳይታቸው ላይ ባወጡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ከታኅሣስ አንስቶ ተገድለዋል ያሏቸው 140 ሰዎች ጉዳይ ጠበቅ ተደርጎ እንዲያዝ ነው የጠየቁት፡፡

ሲቪከስ
ሲቪከስ

የኦሮምያው አለመረጋጋት የተጫረው ኅዳር 2/2008 ዓ.ም ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ በሚገኝ የኦሮምያ ክልል ሥፍራ የአንድ ትምህርት ቤትና ደን ይዞታዎች ለግል ባለሃብት መሰጠታቸውን ተመቃወም የአባባቢው ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ ባደረጉበት ወቅት እንደነበር የሲቪከስና የአምነስቲው መግለጫ አስታውሶ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ተቃውሞዎቹ በይዘትም በስፋትም እያደጉ መምጣታቸውን ተናግሯል፡፡

ተቃዋሚዎቹ መንግሥት ባወጣው የተቀናጀ ልማት ዕቅድ ‘አዲስ አበባ ወደ ኦሮምያ እየተስፋፋች ትሄዳለች’ የሚል ሥጋት ማንሣታቸውን መግለጫው ተናግሯል፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል
አምነስቲ ኢንተርናሽናል

ሰልፎቹና የአደባባይ ተቃውሞዎቹ ወደ ኃይልም እየተለወጡ ብዙ ሰልፈኞች መገደላቸው፣ ብዙዎቹ የሰልፎቹ ተሣታፊዎችና የተቃዋሚዎች መሪዎች መታሠራቸውንም ጠቁሟል፡፡

መንግሥት የማስተር ፕላኑን ዕቅድ መሠረዙን ማክሰኞ፤ ጥር 3/2008 ዓ.ም ቢያስታውቅም ተቃውሞዎች ግን በማግሥቱ በአንዳንድ የምዕራብ ሃገርጌ አካባቢዎች፣ በአምቦና በወለጋ አካባቢዎች ተቃዋሚዎች አደባባይ መውጣታቸውን፣ የመንግሥቱ ወታደሮች ጥይት መተኮሣቸውንና ተቃዋሚዎችን መደብደባቸውን መግለጫው አመልክቷል፡፡

በመግለጫው ላይ ቃላቸውን ያሠፈሩት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምሥራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድ እና የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ ዳይሬክተር ሙቶኒ ዋንዬኪ “የፖሊስና የወታደር እርምጃ የተከተለው መንግሥቱ በአመዛኙ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ‘ሽብርተኞች’ ሲል ታኅሣስ 5/2008 ዓ.ም ከጠራ በኋላ ነው” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በኦሮምያ ጉዳይ የሲቪከስና የአምነስቲ መግለጫና አቋም
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG