በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጥያቄዎ መልስ፡ ከዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ እና አቶ ዳንኤል ብርሃኔ


ኦሮምያ ውስጥ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በሰልፈኞችና በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ስለነበረው ግጭትና የመብቶች ጥሰት እጅግ ተፃራሪ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ሪፖርቶችን ወጥተዋል፤ ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ እና አቶ ዳንኤል ብርሃኔ ከአድማጮች ለተነሱ ለጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ፡፡

የሰብአዊ መብቶች ተማጋቹ ዓለምአቀፍ ቡድን ሂዩማን ራይትስ ዋችና በኢትዮጵያ መንግሥት የተቋቋመው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በቅርቡ ኦሮምያ ውስጥ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በሰልፈኞችና በኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ስለነበረው ግጭትና የመብቶች ጥሰት እጅግ ተፃራሪ የሆኑ ሪፖርቶችን አውጥተዋል፡፡በሁለቱ ሪፖርቶች ይዘት ዙርያ አድማጮቻችን ጥያቄዎቻቸውን አድርሰውናል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ቡድኖች በየጊዜው የሚቀርቡበትን የዜጎች መብቶች ጥሰት ክሦች አይቀበልም። እንደ ሂዩማን ራይት ዋች ያሉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች የሆኑ ዓለምአቀፍ ድርጅቶችን “ኔኦ-ሊበራል አጀንዳ ያላቸው” እያለ ሪፖርታቸውን ያጣጥላል።

የገዢው ፓርቲ ፖሊሲ ተቃዋሚዎች የሆኑ ዜጎች ግን በቅርቡ በኦሮምያና በቅማንት እንደተስተዋለው ባለፉት ዓመታትም በአልሞ ተኳሾች እንደሚገደሉ ዘገባዎች ይናገራሉ።

በኢትዮጵያ መንግሥት የተመሠረተው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ለዜጎች መብቶች በፅናት ለመቆም በእውነት ነፃነቱና ብቃቱ አለው?

ሁለት የሕግ ምሁራን፤ አቶ ዳንኤል ብርሃኔ ከአዲስ አበባና ከሜልቦርን አውስትራልያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምሕርት ክፍል ዶ/ር ጸጋዬ አራርሣ ከየበኩላቸው እይታ ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉን ጋብዘናል።

ሙሉውን ዝግጅት ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ለጥያቄዎ መልስ፡ ከዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ እና አቶ ዳንኤል ብርሃኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:55:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG