በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብራስልስ የጸረ-ሽብር ዘመቻ የሽብር ተጠርጣሪዎች ተያዙ


በብራስልስ ቀናት ያስቆጠረው ከፍተኛ ጥበቃና ቁጥጥር በቀጠለበት የቤልጅየም አቃብያነ ሕግ በያዙት የጸረ-ሽብር ዘመቻ በዛሬው እለት አምስት ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ።

በዋና ከተማይቱ ብራስልስ ቀናት ያስቆጠረው ከፍተኛ ጥበቃና ቁጥጥር በቀጠለበት የቤልጅየም አቃብያነ ሕግ በያዙት የጸረ-ሽብር ዘመቻ በዛሬው እለት አምስት ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ። እርምጃው እስካሁን የተያዙትን የሽብር ተጠርጣሪዎች ቁጥርም 21 አድርሶታል።

አቃብያነ ሕጉ ዛሬ ይፋ እንዳደረጉት ፖሊስ በብራስልስ ባካሄዳቸው 22 አሰሳዎች 16 የሽብር ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን በፓሪሱ የሽብር ጥቃት ዋናው ተጠርጣሪ ሳልህ አብደልሰላም አሁንም ግን ያለበት አልታወቀም።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተንቀሳቀሰበትና እርምጃዎቹን በወሰደባቸው ጊዜያት አንድ ተጠርጣሪ መቁሰሉን ባለሥልጣናቱ ይፋ አድርገዋል።

“የፓሪሱን መሰል የአሸባሪዎች ጥቃት እንዳይደርስ ስጋት አለን፤” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቻርልስ ማይክል ትላንት እሁድ ተናግረዋል።

ዋናው ተጠርጣሪ ሳልህ አብደልሰላም ባለፈው ሕዳር 4 ቀን ጽንፈኛው እስላማዊው ቡድን አሸባሪዎች ፓሪስ ላይ ከ130 በላይ ሰዎች የተገደሉበትንና ብዙዎችን ያቆሰሉበትን የተቀነባበረ የሽብር ጥቃት ካደረሱ ጥቂት ሰዓታት በኃላ ድንበር ተሻግሮ ወደ ቤልጂየም መግባቱ ይታመናል። ዝርዝሩን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

በብራስልስ የጸረ-ሽብር ዘመቻ የሽብር ተጠርጣሪዎች ተያዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:11 0:00

XS
SM
MD
LG