በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦጌ ተሸለመች


ዶክተር ቦጋለች ገብሬ - ቦጌ
ዶክተር ቦጋለች ገብሬ - ቦጌ



please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
ዶክተር ቦጋለች ገብሬ - የኬጂኤም-ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ
ዶክተር ቦጋለች ገብሬ - የኬጂኤም-ኢትዮጵያ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ
ቀድሞ “ከምባቲ ሜንቲ ጌዝማ” ተብሎ ይታወቅ የነበረው ባሁን መጠሪያው ኬጂኤም-ኢትዮጵያ የሚባለው ድርጅት መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ቦጋለች ገብሬ የቤልጅጉ ንጉሥ ቦዱዪን ድርጅት (ኪንግ ቦዱዪን ፋውንዴሽን)ን የአፍሪካ ልማት ሽልማት አሸነፉ ።
http://www.kbs-frb.be/videoYT.aspx?file=Bogaletch-Gebre,-2012-2013-Winner-of-the&pos=0&id=305629&langtype=1033
ዶክተር ቦጋለች በተለያዩ ሥር የሰደዱ ባህላዊ እና ልማዳዊ ችግሮች ዙሪያ ማኅበረሰቦች ያላቸውን አመለካከት በመቀየር የሴቶችን ኑሮ ለማሻሻል ለዓመታት ባካሄዱት ትግል እና ባስመዘገቡት ውጤት የአንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ዩሮ ሽልማት አግኝተዋል።

ዶክተር ቦጋለች ሽልማቱን የተቀበሉት ረቡዕ፤ ግንቦት 14/2005 ዓ.ም ምሽት የቤልጅግ ንጉሥ ዳግማዊ አልበርት እና ንግሥት ፓውላ በተገኙበት በብራስልስ በተካሄደ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ከመሆኑም በላይ ንጉሡ እና ንግሥቲቱ ለአርባ አምስት ደቂቃ ያህል እንዳነጋገሯቸውና የርሣቸው የሴቶችና የማህበረሰቦች ዕድገት ሥልት በሌሎች የተለያዩ ችግሮች ባሉባቸው የአፍሪካ ኣካባቢዎች በሥራ ላይ ሊውል ስለሚችልበት መንገድ ንጉሡ ምክር እንደጠየቋቸው ዶክተር ቦጋለች ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG